ከ«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
አንድ ለውጥ 334944 ከ5.107.63.186 (ውይይት) ገለበጠ
መስመር፡ 19፦
=== መካከለኛ ዘመን ===
 
እስላሞች ወደ [[ግብጽ]] ከገቡ በኋላ ከእስክንድርያ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቸገረ። ጸሐፊው አቡ ሳሊኅ በ፲፪ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደ ገለጸው፣ ፓትርያርኩትፓትርያርኩ በየዓመቱ ፪ ደብዳቤዎች ለኢትዮጵያና ለኖቢያ ነገሥታት ይጽፉ ነበር። ይህንን አደራረግ ግን አቡ ሃኪም አስቀረ። ፷፯ኛው ፓትርያርክ ቂርሎስ እንደ ኤጲስ ቆሞስ የላኩት ሰቨሩስ ሲሆኑ የቤተክርስቲያን ሥርዐት ሁሉ እንዲያስጠበቁ ታዘዙ። በ[[1431|፲፬፻፴፩]] ዓ.ም. በዓጼ [[ዘርዐ ያዕቆብ]] ዘመን [[አባ ጊዮርጊስ]] ከአንድ ፈረንሳያዊ ጐብኚ ጋራ ስለ ሃይማኖት ስለተነጋገሩ አንድ ተልዕኮ ወደ [[ሮማ]] ተላከ።
 
በ[[1500|፲፭፻]] ዓ.ም. ደግሞ ኢትዮጵያ ከ[[አዳል]] ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ አንድ አርሜናዊ ወደ [[ፖርቱጋል]] ተልኮ የፖርቱጋል ንጉሥ እርዳታን ለመነ። ስለዚህ በ[[1512|፲፭፻፲፪]] ዓ.ም. የፖርቱጋል ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ። በሚከተለው ክፍለ ዘመን ከፖርቱጋል [[ኢየሱሳውያን]] የተባሉ ሚሲዮኖች ቤተ መንግሥቱን ወደ [[ሮማ ካቶሊክ]] ሃይማኖት ለማዞር ብዙ ጣሩ። በመጨረሻ በ[[1617|፲፮፻፲፯]] ዓ.ም. ንጉሥ [[ሱስንዮስ]] ወደ ሮማ ካቶሊክ እምነት ተቀየሩ። ዳሩ ግን የሮማ ሃይማኖት በተዋህዶ ፈንታ ይፋዊ መሆኑን ሕዝቡ በጣም አልወደደምና በ[[1625|፲፮፻፳፭]] ዓ.ም ሱስንዮስ ዘውዳቸውን ለልጃቸው ለ[[ፋሲለደስ]] እንዲሰጡ ተደረጉ። ፋሲለደስ ወዲያው አገሩን ወደ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መለሱ። ከዚህ በላይ በ[[1626|፲፮፻፳፮]] ዓ.ም ፋሲለደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው እንዲሄዱ አዘዙ። በ[[1658|፲፮፻፶፰]] ዓ.ም. መጻሕፍቶቸው እንዲቃጠሉ አዘዙ።