ከ«የላቲን አልፋቤት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 37፦
 
በአንዳንድ መዝገቦች ዘንድ፣ የሮሜ ኬንሶርና አምባገነን [[አፒዩስ ክላውዲዩስ ካይኩስ]] በ320 ዓክልበ. «Z»ን ስላልወደደ ከላቲን ፊደል እንደ ጣለው ይባላል።
 
በ400-300 አክልበ. አካባቢ ጥንታዊ ቅርጾቹ '''𐌇''' /ህ/፣ '''𐌓''' /ር/፣ እና '''𐌖''' /ኡ/ ወይም /ው/፣ በሮማይስጥ እንደ ዘመናዊ ቅርጾቻቸው H, R, V ይጻፉ ጀመር። ከዚያ በኋላ 𐌐 /ፕ/ እንደ ቀድሞ /ር/ «P» ሊጻፍ ቻለ፣ እንዲሁም '''𐌑''' ለ/ሥ/ ስላልጠቀመ የ'''𐌌''' ቅርጽ ወደ «M» ተለወጠ፤ የ'''𐌍''' ቅርጽ ደግሞ «N» ሆነ።
 
በ230 ዓክልበ. ግድም፣ አስተማሪው ስፑሪዩስ ካርቪሊዩስ ሩጋ የ«ክ» ከ«ግ» ድምጽ ለመለየት፣ «C» ትንሽ በመለውጥ አዲስ ፊደሉን «G» እንደ ፈጠረ ይባላል። ከዚህ ጀምሮ C ለ«ክ» ብቻ፣ G ለ«ግ» ብቻ ይበቃቸው ነበር። በዚህ ወቅት ፊደሎች ደግሞ እንደ ቁጥሮች ስላገለገሉ የሌሎቹን ፊደላት ቁጥሮች ለመጠብቅ አዲሱ ፊደል «G» በቀድሞው «Z» ፋንታ በመተካት በ፯ኛው ሥፍራ ተሰካ።