ከ«F» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 22፦
የ«F» መነሻ ከ[[ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት]] «[[ዋው]]» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ [[የግብጽ ሀይሮግሊፍ]] ነበር። ቅርጹ ከዚያ በ[[ፊንቄ]] ([[ከነዓን (ጥንታዊ አገር)|ከነዓን]]) ሰዎች ተለማ።
 
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊ [[ግሪክ አልፋቤት]] ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ። ቅርጹ ትንሽ ተለውጦ ግን ተነባቢውን «ው» ለማመልከት Ϝ ϝ («ዋው» ወይም «ዲጋማ») ተጠቀመ። ከዚህ በኋላ «ው» የሚለው ተነባቢ ከግሪክኛ አነጋገር ስለ ጠፋ፣ «Ϝ ϝ» ለቁጥር (፮) ብቻ ሆነ። (ደግሞ [[ስቲግማ]] ይዩ።)
 
በ[[ኤትሩስክኛ]] ደግሞ «F» ለተነባቢው «ው» ይወክል ነበር። የ«ፍ» ድምጽ ለመወክል «FH» ተጻፈ። በ[[ሮማይስጥ]] ሌላ ምልክት «[[V]]» ለ«ው» ስለ ተጠቀመ፣ በላቲን ፊደል ፊደሉ «F» ለ«ፍ» ሊወክል ጀመር።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/F» የተወሰደ