ከ«ሳይንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ሳይንስ''' የሚለው ቃል ከ[[ላቲን]] ''scientia'' (/ስኪየንቲያ/)<ref>«ሳይንስ» የሚለው አጠራር ከ[[እንግሊዝኛ]] ነው፤ ለዚሁም አጠራር ታሪካዊ ምክንያት በተጨማሪ [[C]]ን እና [[ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ]]ን ያንብቡ።)</ref> የመጣ ሲሆን ትርጉሙም «ዕውቀት» ማለት ነው። ሆኖም ግን በአሁኑ ዘመን ሳይንስ ማለት ዕውቀት ማለት አይደለም። ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ነው እንጂ ሁሉ ዕውቀት ሳይንስ አይደለም። ፍልስፍና ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ምንም እንኳ ዕውቀት ቢሆንም። ሂሳብ ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ዕውቀት ይሁን እንጂ።
 
ሳይንስ ማለት በተግባር ሊፈተኑ በሚችሉ ማብራሪያወችና እንዲሁም ትንቢቶች መንገድ እውቀትን የሚገነባ እና የሚያደራጅ መዋቅር ነው። <ref>http://www.m-w.com/dictionary/science</ref> «ሊፈተን የሚችል» ሲባል እውነትነቱ ሊረጋገጥ የሚችል ማለት ሳይሆን ውሸት አለመሆኑ ሊረጋገጥ የሚችል ማለት ነው። በሁለቱ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፣ ሳይንስን ከሃይማኖትና ከሌሎች የዕውቀት ዘርፎች የሚለየው ይህ ወሳኝ ልዩነት ነው።
 
ሳይንስ ባጠቃላይ መልኩ የ[[ሳይንሳዊ ዘዴ]] ተብሎ የሚታወቀውን የምርምር መንገድ ይከተላል። መንገዱ በራሱ ገጽ ላይ የተብራራ ስለሆነ እዚህ ላይ መመለስ አያስፈልግም።
 
== ግርጌ ነጥቦችና ዋቢ ጽሁፍ ==
<references/>