ከ«ሙሴ ቀስተኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

916 bytes added ፣ ከ4 ዓመታት በፊት
ሙሴ ቀስተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ከ አድዋ ጀምሮ እስከ ፋሽሽት ወረራ ድረስ ለአርባ ዓመታት ትልቅ ሚና የተጫወተ፣ እንደውም ታሪኳም የነበረ ሰው ቢሆንም በትውልድ አገሩ ኢጣልያም ቢሆን በሚስቱና የልጆቹ አገር ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ‘ብቅ፣ ጥልቅ’ ከማለት በስተቀር እምብዛም ስለሱ የተጻፈ ነገር የለም።
 
ከአድዋ ጦርነት በኋላ በምርኮኝነት ኢትዮጵያ ላይ ይቅር እንጂ ከዚያ በኋላ ኑሮውን እዚያው ያደረገው በውዴታ ይሁን በግዴታ አይታወቅም። እጃንሆይ ምኒልክስ ዘንድ በማን አስተዋዋቂነት/አቅራቢነት ኖሯል የአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ዕቅድ ለመንደፍ የበቃው? በሕዝብ የሥራ ሚኒስቴር ውስጥ ዲሬክቶር በነበረበት ጊዜ ሌላ በሙያው የሠራቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ከራስ ደስታ ዳምጠው አክስት ጋር ለጋብቻ የበቃውስ በምን ሁኔታ ነበር? እነኚህንና የመሳሰሉ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል።
ኢትዮጵያዊው ምሁር መርሳዔ ኀዘን ወ/ቂርቆስ (18 91 -1971 እ.ኢ.አ.) “ትዝታዪ ስለ ራሴ የማስታውሰው“ በሚለው የህይወት ታሪክ መፅሀፋቸው፤ ሙሴ ቀስተኛ ከሌላ ጣሊያናዊ ቴንቲኒ ባንዲ ከተባለ ጋር በንጉስ ዳግማዎ ሚኒሊክ ዕቅድ ከአዲስ አበባ እስከ አዲስ ዐለም ያለውን መንገድ በድንጋይ ንጣፍ ለማልበስ የቅድመ ምርመራ “survey “ስራውን እንደሰሩ ማወቃቸውን ተርከዋል በሌላ መፅሀፍ የወቅቷን አዲስ አበባ በፎቶግራፍ በሚያሳይ መፅሀፍ ኢጣሊያዊው መሀንዲስ ቀስተኛ ወደ እንጦጦ ማርያም ቤተ/ክርስቲያን የሚያመራውን የመንገድ ስራ በበላይነት ቀጥጥር ላይ እንደተሳተፍ ተገልፆል፡፡
 
==ማገናዘቢያ==
29

edits