ከ«ብራና መቅደስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 4 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q2210843 ስላሉ ተዛውረዋል።
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ብራና መቅደስ''' በ[[ሞትሙት ባሕር ብራናዎች]] መኃል አንድ ነው። ይህ ብራና ጥቅል በ[[1948]] ዓ.ም. በዋሻ ቢገኝም እስከ [[1959]] ዓ.ም. ድረስ በሊቃውንት አልተተረጎመም ነበር። የተጻፈው በ[[ዕብራይስጥ]] ሲሆን ስለ[[ቤተ መቅደስ]] የሚነኩ የ[[እግዚአብሔር]] ትዕዛዛት ለ[[ሙሴ]] ይከትታል።
 
በነዚህ ትእዛዛት የዘላለማዊ ቤተ መቅደስ ዝርዝሮች፣ ሥርዓቶችና ደንቦች ለሙሴ ይገለጻሉ። ሆኖም በታሪክ የ[[እስራኤል]] ንጉስ [[ሰሎሞን]] ቤተ መቅደስ በ[[ኢየሩሳሌም]] በሠሩ ጊዜ፣ አሠራሩ በዚህ አይነት እቅድ አልነበረም። በዚህ ብራና የተገለጸው ቤተ መቅደስ ገና መቸም አልተሠራም። ቤተ መቅደሱ በዚህ የተሰጠው መጠን በነቢዩ [[ሕዝቅኤል]] ራዕይ ከታየው ቤተ መቅደስ መጠን ይልቅ ይበልጣል (''[[ትንቢተ ሕዝቅኤል]]'' ምዕ. 40-47)። በምዕራብ ሊቃውንት አስተያየት ዘንድ፣ ያልታወቀ ደራሲ፦ «የኢየሩሳሌም መቅደስ እንደ ሰሎሞን መቅደስ ሳይሆን እንዲህ መሆን ነበረበት» የሚል ሀሣብ ለማቅረብ ፈልጎ ነበር።