ከ«የቅሌምንጦስ ስነ ጽሑፍ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ስኅተት
No edit summary
መስመር፡ 9፦
በዚያው ዓመት ከይሁዳ ወደ ሮሜ የደረሰው ሰው ሁሉ እንዲህ አይነት ወሬ ስለ ደገመው፣ በተለይም በቅንነት እንጂ በጠማማነት እንዳልተናገሩ ስለ መሠላቸው፣ የሮሜ ኗሪዎች ከነቅሌምንጦስ እጅግ ሲገርሙ፣ በዓመቱም ውስጥ [[ባርናባስ]] የተባለው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር በሮሜ ደርሶ በአደባባይ ስለክርስቶስ አዋጀ፣ እንዲህ ብሎ፦
 
:«ስሙኝ፣ እናንተ የሮሜ ዜጎች ሆይ። የእግዚአብሔር ልጅ አሁንም በይሁዳ ክፍላገር አለ፤ ለሚሰሙትም ሁሉ የዘለዓለማዊ ሕይወት ተስፋ ቃል ይሰጣል፤ ሆኖም ተግባሮቹን እንደ ላከውም፣ እሱም እግዚአብሔር አብ፣ ፈቃድ መሠረት ለማስተዳደር አስፈላጊ ይሆንበታል። ስለዚህ ከክፋት ወደ በጎነት፣ ከኅልፈታዊ ወደ ዘላቂው ዞራችሁ፣ አንድ አምላክ ብቻ፣ የሰማይና የምድር ገዥ መኖሩ፣ በጽድቅ ዓይኖቹ ፊት እናንተ ኃጥአን በዓለሙበእርሱ ዓለም መኖራችሁን፣ እወቁ። ብትቀይሩ ግን እንደ ፈቃዱም ብትሠሩ እንደ ሆነ፣ እንግዲህ ወደ መጪው ዓለም መጥታችሁ፣ ሕያዋን ሆናችሁ፣ የማይናገር በረከትና ዋጋ ታገኛላችሁ።»
 
ከሮሜ ሕዝብ አንዳንዱ ባርናባስን ቢከራክረው ቅሌምንጦስ ግን ሰምቶት በመከታው ድምጹን አነሣ። ከጊዜ በኋላ ባርናባስ ወደ ይሁዳ ተመለሰና ቅሌምንጦስ ደግሞ በተረፈ ለመረዳት እራሱ ወደ ይሁዳ ተጓዘ። እዚያ ስምዖን ጴጥሮስን አገኝቶ አሁን ከ[[ትንሳኤ]] በኋላ ስለ ሆነ ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ስብከት፣ ስቅለትና ዕርግት ለቅሌምንጦስ አስረዳ።