ከ«ጋሜር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
የ[[አይሁድ]] ታሪክ ጸፈፊ [[ዮሴፉስ]] ([[1ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም.) እንዳለው፣ «ጎሜር ግሪኮች አሁን '[[ገላትያ]]ውያን' የሚሏቸውን፣ በድሮ ግን 'ጎመራውያን' የተባሉትን ሰዎች የመሠረተ ነበር።»<ref>ፍላቪዩስ ዮሴፉስ፣ ''የአይሁዶች ጥንታዊነቶች'', I:6.</ref> በእርግጥ የገላትያ ስም የመጣ በዚያ አገር ከሰፈሩት [[ጋሊያ]]ውያን ([[ኬልቶች]]) ነበረ። ዳሩ ግን [[አቡሊድስ]] የተባለው ክርስቲያን ሊቅ (226 ዓ.ም. ግድም) ጎሜር የ[[ቀጴዶቅያ]]ውያን አባት እንደ ሆነ ጽፏል።<ref>''Chronica'', 57.</ref> [[ሄሮኒሙስ]] (380 ዓ.ም. ግድም) እና [[ኢሲዶር ዘሰቪል]] (590 ዓ.ም. ግድም) ግን የዮሴፉስን ቃል ተከትለው የጎሜርን መታወቂያ ከገላትያን፣ ጋሊያውያንና ኬልቶች ጋራ አንድላይ አደረጉ።
 
በአሁኑ [[ዩክራይን]] በጥንት የኖረው [[ኪመራውያን]] (ወይም ጊመራውያን፣ ሲሜራውያን) ሕዝብ ከ700 ዓክልበ. በኋላ ወደ እስያ ወርረው ከ[[አሦር]] መንግስት ጋራ ተጣሉ። እነዚህ የጎሜር ዘሮች እንደ ተቆጠሩ በሰፊ ይታስባል፤ ለምሳሌ በ[[አማርናአማርኛ]]ው «''መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋራ''» ስለ ጋሜር እንዲህ ይላል፦ «የጋሜር ሕዝቦችና ነገዶች በ[[ጥቁር ባሕር]] አካባቢ ይኖሩ ነበር (በኋላ ሲሜራውያን ወይም ጋሜራውያን ተብለዋል)።»
 
ከዚህ በላይ በ200 ዓክልበ. ግድም በአሁኑ [[ዴንማርክ]] የኖረ [[ኪምብሪ]] ሕዝብ ከዩክራይኑ ኪሜራውያን ጋር አንድላይ እንደነበሩ ከጥንት ጀምሮ ተብሏል። ይህ ኪምብሪ ሕዝብ መጀመርያ ከኬልቶች ወገኖች ጋር ተቆጠረ፣ በኋላም ከጀርመናውያን ወገኖች መካከል ተገኙ። በ[[1578]] ዓ.ም. የ[[እንግላንድ|እንግሊዝ]] ታሪክ ጸሐፊ [[ዊሊያም ካምደን]] ባሳተመው መጽሐፍ ዘንድ፣ እነዚህ ''ኪምብሪ'' እና ''ኪመራውያን'' የጎሜርን ስም ሲጠብቁ፣ የኬልቶችም አባቶች ሲሆኑ፣ ይህን የሚያመልከት እስከ ዛሬ ድረስ የ[[ዌልስ]] ኗሪዎች በራሳቸው ቋንቋ «ኪውምሪ» መባላቸው ነው አለ።<ref>[http://www.visionofbritain.org.uk/text/chap_page.jsp;jsessionid=0CC4D5FD7805C8042FA29B9063F849DD?t_id=Camden&c_id=2 Camden's ''Britannia''], I.17,19.</ref>.