ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 65፦
፱. ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከነፃነትዋ ጋር ጠብቃ ያቆየቻቸው ቋንቋዎችዋና የተሟሉት ቀለምዎችዋ ዛሬም በእኩልነት እያንዳንዱ ቀለምዋ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተብ ተደርጎ ተከባብሮና ተጋብቶ የኖረው ሕዝብ ፍላጎትና እኩልነት በኣብሻ ሥርዓት ቴክኖሎጂ ምሳሌ በግዕዝኤዲት ቀርቧል። የኣንዳንዶቹን ኣንድ ቋንቋ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች የሌላውን በስድስት መክተብ ወይም እንደሌሉ መርሳት የለም። ፲. የምሑራንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ሥራና ጥቅም ለኣለ ችግር መፍትሔ መፍጠር ነውና ዶ/ር ኣበራ ለእነዚያ የሚጠቅሙ ሠርተዋል። ኣንዳንድ የግዕዝ ተመራማሪዎች ግን በተሳሳተ ዓላማቸው ፊደሉ ለላቲን ፊደልና ገበታ እንዲስማማ መክተቢያ ሴራ መፍጠር ስለሆነ ግዕዝኤዲት ሳይንሳዊ ዓላማን በመሳት እንዳይቀጥሉ ትክክለኛውን ኣስተሳሰብ ያስገነዝባል። በቅርቡ ኣንድ የፈጠራው ትክክለኛ ኣከታተብ የገባቸው ኢትዮጵያዊ “ዶ/ር አበራ ምሥጋና ይግባውና የአማርኛ ጽሑፍ ትየባ ፍጥነቴ ከእንግሊዝኛው አያንስም” በማለት ጽፈዋል። ፲፩. ግዕዝኤዲት በዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣከታተብ ለመማር ይጠቅማል። በዓማርኛ በብዛት የምንጠቀምባቸው ቀለሞች ሳድሳን ስለሆኑ በኣንድ መርገጫ ይከተባሉ። በብዛት ኣጠቃቀም ሁለተኛ የሆኑት ለሁለቱ ዝቅ መርገጫዎች ተመድበዋል። ለግዕዝ ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ላይ በነፃ ለመማርያ የቀረቡ እንግሊዝኛ ኣከታተብ መለማመጃዎችን በመጠቀም ያለኣስተማሪ በፍጥነት መክተብ መማር ይቻላል። "አ"፣ ሰ"፣፣ ደ" እና "ፈ" በግራ እጅ ጣቶች "ጀ"፣ "ከ"፣ "ለ" እና "ጠ" በቀኝ እጅ ጣቶች ይከተባሉ። ምሳሌ [http://www.youtube.com/watch?v=vXsutlz0GIQ] ፲፪. ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትና የታገሉለት ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስላገኘ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል እንዲቀር ቢጻፍም ዓማርኛ ነው ብለው ሲያቀርቡ የነበሩና ዛሬም የሚያቀርቡ ኣሉ። [http://archive.is/No43M] ግዕዝኤዲት የሚሠራው በትክክለኛ የግዕዝ ፊደላት ስለሆነ ልዩነቱን የማያውቁ እንዳይታለሉ ይጠቅማል።
 
፲፫. የግዕዝና ላቲን ኣከታተብ ግንኙነት የላቸውም። በጥቂት የላቲን ቀለሞች እስፔሊንግ ብዙ የሆኑትን የግዕዝ ቀለሞች መክተብ መሞከር ላቲኑን ለመጥቀም ወይም ግዕዝን ለማዳከም ካልሆነ ጥቅም የለውም። ግዕዙን በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ኣለባችሁ ብሎ ኢትዮጵያውያንን ያስገደደ የለም። በላቲን “b” እና “o” ሲረገጡ “bo” ይታያሉ። በግዕዝ “bo” ሲርገጡ “ቦ” ቀለምን ሊያስከትቡ ይችላሉ። “bo” ማለት “ቦ” ኣይደለም። እንዲሁም “ቦ” “bo” ኣይደለም። በ”ቦ” ምትክ “bo” እየጻፉ የዓማርኛውን ቀለም ትተው ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ተጠቃሚዎች ቍጥር እየጨመረ ነው። [http://www.aklweb.com/forum/index.php?PHPSESSID=e21d4c881616b165bac97be3ddf04389&action=printpage;topic=206.0] [http://mahiberekidusan.org/Default.aspx?tabid=88&ctl=Details&mid=371&ItemID=553] ይህ የዓማርኛ ቁቤ ስለሆነ ፊደሉንና ቋንቋውን ሊያዳክማቸው ይችላል። [https://www.facebook.com/permalink.php?id=380157832031351&story_fbid=564754706904995] [http://ethiozeima.com/2010/02/] [https://www.facebook.com/tasteoflove/posts/464517913609102] ተጨማሪ ምሳሌ ካስፍለገ ኣንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓማርኛ በላቲን ፊደል እንዲጻፍና በኣጻጻፉም በግዕዝ ፊደል ምትክ በላቲን ፊደል ጽፎ ያቀረበው ጽሑፍ በዓማርኛው በዓማርኛና ዓማርኛው በእንግሊዝኛ እዚህ [http://mahiberekidusan.org/Default.aspx?tabid=88&ctl=Details&mid=371&ItemID=553] ኣለ። ዓማርኛን በላቲን ፊደል መጻፍና ማንበብ በኣንድ በኩል ዓማርኛንና ፊደሉን ማዳከም ሲሆን በሌላ በኩል ደካማና ኣክሳሪ የላቲንን ፊደል በዓማርኛው ፊደል መተካትን ለማስፋፋት ይመስላል። ይኸን ኣጠቃቀም ዶክተሩ ከሚቃወሙባቸው ምክንያቶች መካከል ዓማርኛን በላቲን ቀለሞች መክተብ ከዓማርኛው ቀለሞች የበዙ ቀለሞችን መጠቀምን ስለሚያስከትል ነው። "የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር" የሚለውን ርዕስ በ15 የግዕዝ ቀለሞች ማስፈር ሲቻል "yeityoPya yezemen aqoTaTer" በሚለው 28 መርገጫዎችን በመጠቀም በ24 የላቲን ቀለሞች መተካት ሁለቴ መካሰር ነው። (ይህ ዘዴ ባዶ ስፍራ ቃላት መካከል እያስገቡ በዓማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ የሌለ ኣከታተብን ማስተዋወቅን ቢያስከትልም ይኸንን ኣከታተብ የሚደግፉና እያስፋፉ ያሉ ጥቂት ኣይደሉም።) ግዕዝኤዲት የሚከትበውም ከእዚያ በኣነሱ መርገጫዎች ነው። ሙሉ ጽሑፉን በላቲን ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በዓማርኛ ፊደል ማስፈር ብዛቱን ወደ 64.7 በመቶ ዝቅ ያደርገዋል። ይህ ውጤት በደካማ ኣከታተብ ዓማርኛና እንግሊዝኛውን ፊደላት ስናወዳድር ነው። በግዕዝኤዲት ኣከታተብ ይኸው ጽሑፍ በዓማርኛ የሚከተበው በኣነሱ መርገጫዎች ስለሆነ ከኣብሻ ኣከታተብ የተሻለ ኣከታተብ በኣሁኑ ጊዜ የለም። ይህ ለዓማርኛው ሲሆን ሌሎች የግዕዝ ፊደላት ሲጨመሩ ለእስፔሊንጉ ተጨማሪ መርገጫዎች ለሌላው ዘዴ ስለሚያስፈልጉ ግዕዝኤዲት ተወዳዳሪ የለውም። ለምሳሌ ያህል በሌላ ዘዴው እስፔሊንግ የዓማርኛው "ፄ" የሚከተበው በስድስት መርገጫዎች ስለሆነ ለጉሙዙ "ጼ" መክተቢያ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። ስለዚህ ትርፉ እጅ ማሳመም ነው። [http://h-net.msu.edu/cgi-bin/logbrowse.pl?trx=vx&list=h-africa&month=9710&week=c&msg=VigErqFCLyUPvfsoCwFZkw&user=&pw=] ግዕዝኤዲት የዓማርኛውን ሆነ የጉሙዙን የሚከትበው በሁለት መርገጫዎች ነው። በሁለት መርገጫዎች መከተብ የሚችልን ኣንድ የግዕዝ ቀለም ከሦስት እንከ ስምንት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ እንዳንሆን ያሰጋል። ፲፬. የተቆራረጡ የአማርኛ የጽፈት መሣሪያ ዓይነት ቀለሞችንና ያልተቆራረጡ ኣንድ የላቲን ፊደል የሚችለውን ቀለሞች እየመረጡና በሌሎች ዘዴዎች ሕዝቡን ሲያጉላሉ ከነበሩት ይገላግላል። ፲፭. ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ኣያስፈልግም፦ ምሳሌ በማውስ መክተብ። ምክንያቱም ግዕዝኤዲት ባይኖር ኖሮ ግዕዝ ሌሎች ችግሮች ውስጥ ሊወድቅ ይችል እንደነበረ ከእዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሊቀሰቅሱን ይገባል። በእዚህ በተራቀቀው የኮምፕዩተር ዘመን የግዕዝ ፊደል በሳይንስና ቴክኖሎጂ [http://archive.is/LWaLI] ተደግፎ ማደግ ያለበት ጊዜ ነው።
 
ፓተንት እየተጠበቀ ወይም Patent Pending የሚለው ማሳሰቢያ ነፃው ግዕዝኤዲት ላይ ያለውና እዚህም ስለሚሸጠው ዓይነት ገለጻም ውስጥ የተጠቀሰው ሌላ ሰው በተሰጠው ወይንም በተሸጠለት እንዲጠቀም እንጂ ዘዴውን መገልበጥ ትክክል እንዳልሆነና በሕጉ መሠረት እንደሚያስቀጣም ለማስጠንቀቅ ነው። የፈጠራውን እንግሊዝኛ ገለጻ በቍጥሩ US20090179778 [http://appft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO2&Sect2=HITOFF&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsearch-bool.html&r=1&f=G&l=50&co1=AND&d=PG01&s1=Aberra&s2=Molla&OS=Aberra+AND+Molla&RS=Aberra+AND+Molla] ወይም በሚከተለው ማያያዣ http://appft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO2&Sect2=HITOFF&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsearch-bool.html&r=1&f=G&l=50&co1=AND&d=PG01&s1=Aberra&s2=Molla&OS=Aberra+AND+Molla&RS=Aberra+AND+Molla ማግኘት ይቻላል። ፈጠራው መጀመሪያ የቀረበውና ያተመው የዩናይት እስቴትስ መንግሥት ስለሆነ ከኢትዮጵያው ቅድሚያ ኣለው።