ከ«መደብ:የትራንስፖርት ሚኒስቴር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ ለሚመለከተው ሚኒስተር መስሪያ ቤት አገራችን...»
 
ጽሑፉን በሙሉ ደመሰሰ።
መስመር፡ 1፦
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ
የቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ
ለሚመለከተው ሚኒስተር መስሪያ ቤት
 
አገራችን በትራፊክ አደጋ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ሀገራት ተርታ መሰለፏ ይታወቃል፡፡ እንዲያውም ብዙዎቻችን ተጋኖ ስንሰማው ወይም ስናራግበው የኖርነው በትራፊክ አደጋ አገራችን ኢትዮጵያ የሪከርድ ባለቤት እንደነበረች ነው፡፡
ሆኖም ሰሞኑን ይህን ለማረጋገጥ መረጃዎችን ከኢንተርኔት ሳፈላልግ የትራፊክ አደጋ የሪከርድ ባለቤቷ አፍሪካዊቷ ናሚቢያ መሆኗን ተረዳሁ፡፡ አንፃራዊ እፎይታ ባገኝም ግን አገራችን ኢትዮጵያ ሪከርዱን ትነጠቅ እንጂ በትራፊክ አደጋ በግንባር ቀደምትነት ተርታ መሰለፏን እንዳስጠበቀች መሆኑን ካገኘኋቸው የመረጃ ምንጮች ላረጋግጥ ችያለሁ፡፡
በዓለም ጥናት ከተደረገባቸው 193 ሀገራት ኢትዮጵያ በ20ኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው፡፡
ሸገር በመባል የሚታወቀው የሬዲዮ ፕሮግራም ሁሌ ጠዋት ላይ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ብቻ የደረሱ የትራፊክ አደጋዎችን በሰው እና በንብረት በሚል እና የአደጋውን ዓይነት ቀላል፣ ከባድ በሚል በመለየት በየቀኑ ስንት ወገኖቻችንን እንዳጣን መርዶ ያረዳናል፡፡ የመርዶው ዜና ምንጭ ደግሞ ሳጅን አሰፋ መዝገቡ እንደሆኑ በቀጥታ በማቅረብም ይሁን ከእሳቸው የተገኘ መረጃ እንደሆነ በማከል፡፡፡ የመርዶ ዜናው ምንጭ ሳጅን አሰፋ መዝገቡም ይሁኑ የእሳቸው ምክትል ወይም ሌላ ትራፊክ ፓሊስ ዜና አንባቢውም ማን ይሁን ማን፤ የሬዲዮ ስርጭቱም በሸገርም ይሁን በFM በሬዲዮ ፋና ወይም በኢትዮጵያ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን እሱ አይደለም ጭንቀቴ እና የዚህች ፅሑፍ ማጠንጠኛዬ፡፡
በየጊዜው በዚህ የትራፊክ አደጋ ዙሪያ በቀጥታ የስራ ፀባያቸው የሚመለከታቸው ግለሰቦች እየተጋበዙ ውይይት እንደሚያደርጉ በተለይ በኢትዮጵያ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን ቴሌቭዥን ሁሌ ሰኞ ሰኞ ጠዋት ላይ በሚተላለፈው ፕሮግራም የሚደረጉ ውይይቶችን እከታተላለሁ ውይይቱ አደጋውን በመቀነስ ገረድ ግን ምንም ያህል ለውጥ አላመጣም፡፡
በተለይ በአንድ ወቅት ሚኒባስ፣ ዶልፊን በተለምዶ አባ ዱላ በመባል የሚጠሩ አነስተኛ አውቶብሶች ከተፈቀደላቸው 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ውጭ እስከ 540 ኪ.ሜ እና ትርፍም ጭነው በሌሊት የቸኮሉ መንገደኞችን አሳፍረው ሲሄዱ ስንት ወገኖቻችን ናቸው ለቸኮሉበት ጉዳይ ሳይደርሱ ካልቸኮሉበት የወዲያኛው ዓለም የሄዱት፡፡
ባለፈው ዓመት ይሁን በዚህ እያገባደድነው ባለነው ዓመት ዕርግጠኛ አይደለሁም ብቻ እነዚህ አደጋ እያደረሱ ያሉ ሚኒ ባሶችን ለመቆጣጠር የተደረገን ውይይት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ተከታትያለሁ፡፡ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ስልቶችንና የመፍትሄ ሀሳቦችን የውይይት ተሳታፊዎች ሲያቀርቡ ሰምቻለሁ፣ አይቻለሁ፡፡
 
የቀረቡት የመፍትሄ ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው የሚጠበቀውን ለውጥ ግን እንዳላመጡ በቅርብ እኔው እራሴ በጣም አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ ከሀዋሳ ሻሸመኔ በአንድ አቀባባይ ሚኒባስ ከሻሸመኔ አዲስ አበባ ደግሞ ዶልፊን በሚባል ሚኒባስ ሌሊቱን ተጉዤ አዲስ አበባ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እግዚያብሄር ተብቆኝ በሰላም ደርሻለሁ፡፡ በተወያዮች ከስምምነት የተደረሰባቸው ስልቶችና መፍትሄዎች ሚኒ ባሶችን መቆጣጠር እንዳልቻለ እንዲሁም ለእኛ ለመንገደኞች የሰጡት ምክረ ሀሳብም ስላልሰራ እና ሌላ አመራጭ ስላጣሁ በህይወቴ ፈርጄ ከእነዚህ ህገ-ወጥ ሚኒባሶች በአንዱ ሄድኩ፡፡
በዚህች ፅሑፌ የምታውቁትን ከላይ የገለፅኩትን ላካፍላችሁ ሳይሆን የፈለግሁት በቅርብ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ናይሮቢ ለስራ ሄጄ አምስት ቀናት በቆየሁበት ከፍተኛ አውቶብሶች 24 ሰዓት ማለትም ቀንና ሌሊት መደበኛ አገልግሎት ሲሰጡ ስመለከት ወዲያው የትራፊክ አደጋ መቀነሻው የመፍትሄ ሀሳብ መጣልኝ፡፡ በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከደርግ ጋር የነበረውን ትግል እሳቸው እና ሌሎች የትግል ጓዶቻቸው እንዴት እንደተቀላቀሉ ሲናገሩ ያሉት ትዝ አለኝ፡፡ ምንድነው ያሉት እጠቅሳለሁ “መውጫ በሩም ሆነ መስኮቱ ክርችም ብሎ ከተዘጋብህ ግርግዳውን ቀደህ ለመውጣት ትሞክራለህ”:: አገር አቋራጭ ከፍተኛ አውቶብሶች መብራት እንደሌላቸው ቀን ብቻ ነው አገልግሎት መስጠት ያለባቸው ተብሎ ስምሪቱ ቀን ብቻ መሆኑ ያመጣው ስህተት እንደሆነ ትንንሽ አውቶብሶች ህግ እንዲጥሱ እኛም አስቸኳይ ጉዳይ ስላለን፤ ለሌላ ዘመድ ወዳጅ ለቀብር ለመድረስ የቸኮሉ የእራሳቸውን ቀብር ለማፍጠን የተገደዱት፤ ሌሊቱን ተጉዘን እንድረስ በሚል አደጋ ሊገጥም እንደሚችል እየተገመተ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያፈልቅ ጠፍቶ ወይም የጎረቤት ሀገራትን ልምድ መውሰድ ሳንችል ቀርተን ስንት ወገኖቻችንን አጣን !!
አገር አቋራጭ ከፍተኛ አውቶብሶች የጊዜ ዕንግዳ እንዲሆኑ እና እንደ ዶሮ መሸት ሲል ወደየማደሪያቸው በመግባት ድምፃቸውን አጥፈተው ለሽ እንዲሉ የተደረገው፣ የተወሰነው ለምን ነው? በዕርግጥ ከ24 ዓመት በፊት
1ኛ አገራቱ ሰላም አልነበረችም፤ የሰዓት ዕላፊ አዋጅም ተጥሎ ስለነበረ
2ኛ የከፍተኛ አውቶብሶች በብዛትም ሆነ በጥራት እንደአሁኑ ስላልነበሩ
አውቶብሶች የግድ ቀን ላይ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደረገ፡፡
አሁን ግን ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ያሉ አይመስለኝም፡፡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሰላም ነው፣ የሰዓት ዕላፊ አዋጅም የለም፣ የከፍተኛ አውቶብሶች ዕጥረትም የለም እንዲያውም ትኬት ቆራጮች ከእኔ ቁረጥ ከእኔ ቁረጥ ለማለት የሚያሰሙትን ጩኸት እና የአውቶብስ ሹፌሮች ድንገት በሞተ ከዳ ወይም በተጨማሪነት መስመር ካገኘሁ በሚል ጠዋት ላይ ከመናኸሪያው ውጭ አውቶብሶች በጣም ረጅም ሰልፍ ይዘው ነው የምናየው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24 ሰዓት አገልግሎት ነው የሚሰጠው፤ እንዲያውም ራቅ ወዳሉ ሀገራት የሚደረጉ ብዙዎች በረራዎች ሌሊት እንደሆኑ ነው የማውቀው፡፡
 
 
የትራፊክ አደጋን ማስቀረት እንኳ አይቻልም፤ መቀነስ ግን ስለሚቻል የኢትዮጵያ ከፍተኛ አውቶብሶች እንደ ኬንያ አገር አቋራጭ አውቶብሶች 24 ሰዓት አገልግሎት ይስጡ፤ በፈረቃ ማለትም የቀን መስመርተኛ እና የሌሊት መስመርተኛ ተብሎ ፕሮግራም ይውጣ፡፡ የሌሊት መስመርተኛ ሹፌሮች ቀን ላይ ይተኙ፡፡ ይህ ከሆነ የቸኮሉ መንገደኞች በእነዚህ ገዳይ ትንንሽ አውቶብሶች መሳፈርን አይመርጡም፡፡ ምክንያቱም ሌሊቱን በከፍተኛ አውቶብሶች ተጉዘው ንጋት ላይ ከፈለጉበት መዳረሻ የሚያደርስ አማራጭ ስለሚኖራቸው፡፡
ስለዚህ በተለይ እነዚህ ገዳይ ትንንሽ አውቶብሶች ያልተፈቀደላቸውን የርቀት ወሰን እና የመጫን አቅም በመተላለፍ የሚያደርሱትን አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የከፍተኛ አውቶብሶችን የአገልግሎት አሰጣጥ በድሮው እና በተለመደው ሁኔታ ቀን ብቻ ከሚሆን ሌሊትም አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መፍትሄ ነው እላለሁ፡፡
 
ተሰማ አያሌው አስረስ
ከዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሰኔ 18/2007 ዓ.ም