ከ«ሳዑዲ አረቢያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
የሣውዲ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡
 
ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ [[ኤዥያ]] ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡
 
አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በእ.ኤ.አ. በ1932 በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስላም ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡