ከ«ካራን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 5፦
እጅግ ጥንታዊ ከተማ ሲሆን በ[[አብርሃም]] ዘመን መኖሩ በ[[ኦሪት ዘፍጥረት]] ይጠቀሳል። የአብርሃም አባት [[ታራ]] ከነቤተሠቡ ጋር ከ[[የከለዳውያን ዑር|ከለዳውያን ዑር]] ከተማ ተነሥተው ሁላቸው ወደ ካራን እንደ ፈለሱ ይላል። የካራን ዙሪያ አገር በ[[እብራይስጥ]] ትርጉም [[ፓዳን-አራም]] (የ[[አራም (የሴም ልጅ)|አራም]] መንገድ) ወይም [[አራም ናሓራይም]] (አራም ከሁለቱ ወንዞች መካከል ወይም [[መስጴጦምያ]]) ይባላል። ካራን በ[[ባሊኅ ወንዝ]] ላይ ነው።
 
ከዚህ በላይ በ[[ኤብላ]] የተገኙት ጽላቶች (23002127-2074 ዓክልበ. ግድም [[ኡልትራ አጭር አቆጣጠር]]) የካራንን ጥንታዊነት ይመሰክራሉ። በነዚህ መዝገቦች መሠረት፣ አንድ የካራን ከንቲባ የኤብላን ልዕልት [[ዙጋሉም]]ን አግብቶ ነበርና እርሷ ከዚያ «የካራን ንግሥት» ተባለች። ካራንም ከዚያ ዘመን ከኤብላ ጋር የሚነግድ ነጻ ከተማ እንደ ነበር ይታወቃል።<ref>''Kazane Hoyuk and Urban Life Histories in Third Millennium Upper Mesopotamia'', Andrew Theodore Creekmore, 2008 p. 93.</ref>
 
ቢያንስ ከ1800 ዓክልበ. ካራን (እንደ ዑር) የጨረቃ ጣኦት የ[[ሲን]] ቤተ መቅደስ መኖርያ እንደ ነበረ በ[[ማሪ]] መዝገቦች ይነገራል። የአራማውያንና ሆራውያን መኖርያ ከ1500 ዓክልበ. በኋላ በ[[ሚታኒ]] (ሃኒጋልባት) መንግሥት ነበረ፤ [[የኬጢያውያን መንግሥት|ኬጢያውያን]] ግን በ1320 ዓክልበ. ግድም አቃጠሉትና ያዙት። ከዚህም በኋላ ዙሪያው በ[[አሦር]] ሥልጣን ውስጥ ሆነ። አሦርም በ[[621 ዓክልበ.]] እየወደቀች ለጥቂት አመታት እስከ [[617 ዓክልበ.]] ድረስ ካራን የአሦር መንግሥት መጨረሻ ዋና ከተማ ሆነ።