ከ«ኤብላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 25፦
 
==የኤብላ ጥንታዊ መንግሥት==
ኤብላ መቼ እንደ ተመሠረተ ባይታወቅም ምናልባት 2350-2400 ዓክልበ. ([[ኡልትራ አጭር አቆጣጠር]]) እንደ ሆነ ሊገመት ይቻላል። የሥነ ቅርስ ሊቃውንት ግን እስከ 3000 ዓክልበ. ድረስ ይገፉታል።
 
በአንዱ ጽላት ላይ ከ[[ኢግሪሽ-ሐላብ]] (2127 ዓክልበ. ግድም) አስቀድሞ የገዙት ፴ ነገሥታት ስሞች ይዘረዝራሉ፦ ሳኩሜ፣ ሹ-[...]፣ ላዳው፣ አቡጋር፣ ናምነላኑ፣ ዱሙዳር፣ እብላ፣ ኩልባኑ፣ አሻኑ፣ ሳሚዩ፣ ዚያሉ፣ ሩማኑ፣ ናማኑ፣ ዳ-[...]፣ ሳጊሹ፣ ዳኔዩም፣ ኢቢኒ-ሊም፣ ኢሽሩድ-ዳሙ፣ ኢሲዱ፣ ኢሽሩድ-ሐላም፣ ኢክሱድ፣ ሪዳ-ሊም፣ አቡር-ሊም፣ አጉር-ሊም፣ ኢቢ-ዳሙ፣ ባጋ-ዳሙ፣ ኤናር-ዳሙ፣ ኢሻር-ማሊክ፣ ቁም-ዳሙ፣ እና አዱብ-ዳሙ ናቸው።
Line 31 ⟶ 32:
 
የተገኙት መዝገቦች ከአዱብ-ዳሙ በኋላ ከገዙት ከሦስቱ መጨረሻ ነገሥታት ዘመኖች ናቸው። እነርሱም [[ኢግሪሽ-ሐላብ]] (12 ዓመታት)፣ [[ኢርካብ-ዳሙ]] (7 ዓመታት) እና [[ኢሻር-ዳሙ]] (35 ዓመታት) ናቸው። ከሃይለኛ ጠቅላይ ምኒስትሮቻቸው የሚታወቁ [[አራኩም]]፣ [[ኤብሪዩም]] እና [[ኢቢ-ዚኪር]] (ወይም ኢቢ-ሲፒሽ) ናቸው።
 
ኢሻር -ዳሙ በማሪ ላይ ከ[[ናጋር]]ና ከ[[ኪሽ]] ጋራ ስምምነት ተዋዋለ፤ አለቃውም ኢቢ-ዚኪር የማሪን ሃያላት በ[[ተርቃ]] ውግያ አሸነፋቸው። ከዚህ በኋላ የኤብላ ሥራዊት [[አርሚ]]ን ያዙ፣ የኢቢ-ዚኪርም ልጅ ኤንዚ-ማሊክ እዝያ ገዥ ተደረገ። ኢሻር-ዳሙ ካረፈ በኋላ ግን ምናልባት 2074 ዓክልበ. ግ. ሳርጎን ወይም ማሪ ኤብላን እንዳጠፋ ይመስላል።
 
ከዚህ በኋላ ኤብላ እንደገና እንደተሠራ ይታወቃል። በ[[ላጋሽ]] ንጉሥ [[ጉዴአ]] ዘመን (2009-1989 ዓክልበ.) በአንዱ ሰነድ ጉዴአ የአርዘ ሊባኖስን ዕንጨት ከኤብላ ግዛት ከ[[ኡርሹ]] ይጠይቃል። በ[[ኡር]] ንጉሥ [[አማር-ሲን]] ፯ኛው ዓመት (1912 ዓክልበ.) የኤብላ ንጉሥ ይጠቀሳል። ከዚህም በኋላ ኤብላ ሁለተኛ ምናልባትም በ[[ሑራውያን]] ዕጅ እንደ ጠፋ ይታሥባል።
 
ዳግመኛም ተሠርቶ በሦስተኛው የኤብላ መንግሥት ወቅት፣ የንጉሥ [[ኢቢት-ሊም]] ሐውልት ቅርስ ተገኝቷል፤ ልክ መቼ እንደ ነገሠ ግን ገና እርግጠኛ አይደለም። የኤብላ ንጉሥ [[ኢመያ]] በ[[ግብጽ]] ፈርዖን [[ሆተፒብሬ]] ዘመን (1806-1803) እንደ ገዛ ከአንድ ሐውልት ቅርስ ታውቋል። በ[[ያምኻድ]] መንግሥት ዘመን ለያምኻድ ተገዥ ነበረ፤ የ[[አላላኽ]] ገዥ [[አሚታኩም]] ልጅ የኤብላን ልዕልት አገባ። [[የኬጥያውያን መንግሥት]] ንጉሥ [[1 ሙርሲሊ]] በ1508 ዓክልበ. ግ. ኤብላንም ያምኻድንም አጠፋቸው። በዚያን ጊዜ የኤብላ መጨረሻ ንጉሥ [[ኢንዲሊማ]] ተባለ።
 
ከዚያ በኋላ በሥፍራው ላይ ጥቃቅን መንደር ብቻ ቀረ፣ ይህም ምናልባት እስከ 500 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ ቆየ።
 
{{መዋቅር-ታሪክ}}