ከ«ኤብላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 28፦
በአንዱ ጽላት ላይ ከ[[ኢግሪሽ-ሐላብ]] (2127 ዓክልበ. ግድም) አስቀድሞ የገዙት ፴ ነገሥታት ስሞች ይዘረዝራሉ፦ ሳኩሜ፣ ሹ-[...]፣ ላዳው፣ አቡጋር፣ ናምነላኑ፣ ዱሙዳር፣ እብላ፣ ኩልባኑ፣ አሻኑ፣ ሳሚዩ፣ ዚያሉ፣ ሩማኑ፣ ናማኑ፣ ዳ-[...]፣ ሳጊሹ፣ ዳኔዩም፣ ኢቢኒ-ሊም፣ ኢሽሩድ-ዳሙ፣ ኢሲዱ፣ ኢሽሩድ-ሐላም፣ ኢክሱድ፣ ሪዳ-ሊም፣ አቡር-ሊም፣ አጉር-ሊም፣ ኢቢ-ዳሙ፣ ባጋ-ዳሙ፣ ኤናር-ዳሙ፣ ኢሻር-ማሊክ፣ ቁም-ዳሙ፣ እና አዱብ-ዳሙ ናቸው።
 
ከነዚህ ስሞች ብዙ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ደግሞ ይገኛሉ፣ በተለይም ከ«ሳጊሹ» እስከ «ኢሽሩድ-ዳሙ»፣ እና «ኤናር-ዳሙ» ያሉት ስሞች ይጠራሉ። ኢቢ-ዳሙ በ[[ካነሽ]] [[ሐቲ]] ከተገኘ ማኅተም ቅርስ ይታወቃል። ቁም-ዳሙ ከሌሎች ሰነዶች ሲታወቅ ከማሪ መንግሥት ጋራ የሆኑት ችግሮች በእርሱ ዘመን እንደ ጀመሩ ይመስላል። ይህም በማሪ ነገሥታት [[ሳዑሙ]] ወይም [[ኢቱፕ-ኢቫር]] ዘመናት እንደ ነበር ይታሥባል። ተከታዩም አዱብ-ዳሙምዳሙ እጅግ አጭር ዘመን እንደ ነገሠ ይታወቃል።
 
የተገኙት መዝገቦች ከአዱብ-ዳሙ በኋላ ከገዙት ከሦስቱ መጨረሻ ነገሥታት ዘመኖች ናቸው። እነርሱም [[ኢግሪሽ-ሐላብ]] (12 ዓመታት)፣ [[ኢርካብ-ዳሙ]] (7 ዓመታት) እና [[ኢሻር-ዳሙ]] (35 ዓመታት) ናቸው። ከሃይለኛ ጠቅላይ ምኒስትሮቻቸው የሚታወቁ [[አራኩም]]፣ [[ኤብሪዩም]] እና [[ኢቢ-ዚኪር]] (ወይም ኢቢ-ሲፒሽ) ናቸው።