ከ«ሉጋልባንዳ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
 
መስመር፡ 5፦
በ«''ሊጋልባንዳ በተራራ ዋሻ''»፣ የኡሩክ ንጉሥ ሆኖ የቀደመው [[ኤንመርካር]] ሠራዊቱን በ[[አራታ]] ላይ እንዲዘመት ያሠልፋል፤ ሉጋልባንዳ ከጦር አለቆቹ አንዱ ነው። ነገር ግን የኡሩክ ሠራዊት ወደ አራታ ሲሄድ በረጅም ተራሮች አልፎ፣ ድንገት ሉጋልባንዳ ተዝለፈለፈ። ሊያንቁት አይችሉምና ጓደኞቹ በዋሻ ውስጥ ከስንቅና ከዕጣን ሙጫ ጋር ይተዉትና መንገዳቸውን ይቀጥላሉ። ሉጋልባንዳ በዋሻው ትንግርት ሕልም ያያልና ይጸልያል፣ የጽሑፉ መጨረሻ ግን አሁን ፍርስራሽ ሆኖ በደንብ ሊነብ አይችልም።
 
በ«''ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ''»፣ ሉጋልባንዳ በ[[ሉሉቢ]] ተራሮች ሆኖ ደብዛው እስካሁን ጠፍቷል፤ ዳሩ ግን ታላላቁ የ«አንዙድ» ወፍ የኤንመርካርን ሠራዊት ዳግመኛ እንዲያገኝ ይረደዋል። የኤንመርካር ሠራዊት አራታን ለ1 አመት ቢከባትም፣ አይከናወንም። ኤንመርካር በኡሩክ መቅደስ ወዳለች ወደ [[ኢናና]] መልዕክት እንዲልክ ተልእኮ ይፈልጋል። ቀድሞ በኤንመርካር መንግሥት 50ኛው አመት [[አሞራውያን|የማርቱ ሕዝብ]] በ[[ሱመር]]ና በ[[አካድ]] በሙሉ በተነሡበት ጊዜ ግድግዳ በበረሃ እንዲሠራባቸው ስለ ረዳችው፣ እንደገና እርዳታዋን አሁን በአራታ ዘመቻው ይጠይቃታል። በመጨረሻ ሉጋልባንዳ ወደ ኡሩክ ኢንዲመልስ ፈቃደኛነቱን ይነግረዋልና መልዕክቱን ለኢናና ያደርሳል። የስዋ መልስ አራታና ምጣኔ ሀብቱ እንዴት እንደሚያዙ የሚል ምስሌምሳሌ ነው።
 
''[[የጊልጋመሽ ትውፊት]]'' በተባለው አፈ ታሪክ ደግሞ፣ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ [[ጊልጋመሽ]] እራሱን «የቅዱስ ሉጋልባንዳና የ[[ኒንሱን]] ልጅ» ይላል። በዚህበዚያ ዘመን፣ ሉጋልባንዳና ሚስቱ ኒንሱን እንደ አማልክት ተቆጠሩ።
 
{{S-start}}