ከ«ፍኖተ ሰላም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 4 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q2354276 ስላሉ ተዛውረዋል።
No edit summary
መስመር፡ 1፦
{{ዋቢ}}
የፍኖተሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ 387 ኪ.ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ 176 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º 41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡:
'''ፍኖተ ሰላም''' (ፍ/ሰላም) በ[[ኢትዮጵያ]] ውስጥ በ[[ጎጃም]] እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ፍኖተ ሰላም ማለት መልካም መንገድ ወይም ጉዞ እንደማለት ሲሆን ይህንንም ስም ያወጡላት [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] እንደሆኑ ይነገራል። ጃንሆይ ከጣሊያን ጦርነት በኋዋላ ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አሁን ፍኖተ ሰላም ያለችበት ቦታ ላይ ከአጃቢዎቻቸው ጋር እረፍት ያደርጋሉ። እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያደረጉት ጉዞም በሰላም የተሞላ ስለነበር ያንን ቦታ ፍኖተ ሰላም ብለው ሰየሙት። ከከተማዋ ወጣ ብሎ የሚገኝ አንድ የዋንዛ ዛፍ ይገኛል። ይህንንም የዋንዛ ዛፍ የተከሉት ንጉሱ ስለነበሩ እስካሁን ድረስ የአባ ንጉስ ዋንዛ እየተባለ ይጠራል።