ከ«አቡነ ባስልዮስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: አዲስ ዘመን - Changed link(s) to አዲስ ዘመን (ጋዜጣ)
No edit summary
መስመር፡ 3፦
'''ቀዳማዊ አቡነ ባስልዮስ''' ([[1884|፲፰፻፹፬]]ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) - [[1963|፲፱፻፷፫]] ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ [[የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን]] ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ።
 
አቡነ ባስልዮስ ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረ ጊዮርጊስ ሲሆን [[መጋቢት ፲፬]] ቀን [[1884|፲፰፻፹፬]] ዓ/ም ከደብተራ ወልደጻድቅ ሰሎሞንና ከወይዘሮ (በኋላ እማሆይ) ወለተማርያም ባዩ በ[[ሸዋ]] አውራጃ ሚዳ ሚካኤል ተወለዱ። ደብተራ ወልደጻድቅ የይፋት ቀውትጌስ ማርያም ተወላጅ ሲሆኑ፣ እማሆይ ወለተማርያም ደግሞ ከመንዝበመንዝ ላሎ ምድር የተወለዱ ነበር።
 
በሕጻንነታቸው ዘመን መንፈሳዊ ትምህርትን እየተማሩና የኮሶ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እያገለገሉ አድገዋል። አቡነ ባስልዮስ የአሥራ-አራት ታዳጊ ወጣት እያሉ በ[[1899|፲፰፻፺፱]] ዓ/ም [[ደብረ ሊባኖስ]] ገዳም ገብተው ትምህርታቸውን ከመምህር ገብረ ኢየሱስ ሲከታተሉ ቆይተው በዚያው ገዳም መዓርገ-ምንኩስናቸውን እስከተቀበሉበት ድረስ ለሦስት ዓመታት በእርድና አገልግለዋል።