ከ«ጥምቀት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 6 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q1133754 ስላሉ ተዛውረዋል።
No edit summary
መስመር፡ 25፦
የኹላችን ሲሳይ»<br />
 
በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩ፣ ቱሪስቶችን መሳቡ አልቀረም። ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ብጫ ያለም ዘር፣ ከ[[አዲስ አበባ]] እስከ [[ላሊበላ]]፣ ከ[[አክሱም]] እስከ [[ጎንደር]] በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው።
 
ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከ[[ጥር ፲፩]] ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ([[ጥር ፲፯]] ቀን) ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በ[[ዮርዳኖስ]] በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ሁነት [[ኢትዮጵያ]] ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የ[[ክርስቲያን]] ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።