ከ«ውክፔዲያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 12፦
 
== የዊክፔዲያ አመሰራረት ==
ዊክፔዲያ ነፃ ኦላይን መዝገበ-ዕዉቀትን (free encyclopedia) ለመፍጠር አላማ አድርጎ የተመሰረተና ቀደም ሲል [[ኑፔዲያ]] (Nupedia) በመባል የሚታወቅ ፕሮጀክት ዉጤት ነዉ። ኑፔዲያ ምንም እንኳን የተሻሻለ የዕርስ-በርዕስ መገማገሚያ (peer review) መንገዶችን አካቶ የያዘና ሙያዊ ብቃት ያላቸዉ መጣጥፍ አቅራቢዎችን የሚጠይቅ ፕሮጀክት የነበረ ቢሆንም መጣጥፎችን አትሞ ለማዉጣት ረጅም ጊዜን ይጠይቅ ነበር። በመሆኑም ይንንም ችግር ለመቅረፍ፣ በ[[2000 እ.ኤ.አ.]] የኑፔዲያ መስራቹ [[ጂሚ ዌልስ]]ና በዚሁ ፕሮጀክት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ [[ላሪ ሳንገር]]<ref>Mike Miliard (March 1, 2008). "Wikipediots: Who Are These Devoted, Even Obsessive Contributors to Wikipedia?". Salt Lake City Weekly. Retrieved December 18, 2008.</ref><ref>Kaplan Andreas, Haenlein Michael (2014) Collaborative projects (social media application): About Wikipedia, the free encyclopedia. Business Horizons, Volume 57 Issue 5, pp.617-626</ref> የተባለ ሌላ ግለሰብ ኑፔዲያን እንደት ማሻሻልና ሌሎች ተጨማሪ ገፅታዎችን አካቶ የሚይዝ ፕሮጀከት ማደረግ እንሚቻል የጋራ ዉይይት አደረጉ።<ref>How I started Wikipedia, presentation by Larry Sanger</ref> በዉይይታቸዉም ወቅት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸዉ አብዛሐኛዎቹ ምንጮች አንድ የዊኪ ድረ-ገጽ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸዉን አስተዋፆ ማበረከት የሚችሉበት መዳረሻ ተደርጎ ድዛይን ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱዋቸዉ። በዚህም መሰረት ማንኛዉም ሰዉ የራሱን አድስ አስተዋፆ ማበርከትና ብሎም ሌሎች የቀረቡ መረጃዎችን ማስተካክልና ማረም እንዲያስችል ተደርጎ ዲዛይን የተተደረገዉ የመጀመሪያዉ የኑፔዲያ የዊኪ ገፅ እ.ኤ.አ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. አየር ላይ ዋለ።<ref>^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.</ref>
 
ነገር ግን ሌሎች የኑፔዲያ ፕሮጀክት አካል የነበሩ አርታኢዎችና ሀያሲዎች በኑፔዲያ ፕሮጀክት ላይ የተደረገዉን የማሻሻያ ለዉጥ በተለየም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸዉን አስተዋሶ ማበርከት የሚያስችልን ድረ ገፅ(ዊኪ) ቅርፅ እዲይዝ ተደርጎ መሻሻሉን በመቃዎማቸዉ፣ የተሻሻለዉ የኑፔዲያ ፕሮጀክት አድስ የስያሜ ለዉጥ በማድረግና “ዊክፔዲያ” በመባል በራሱ አድራሻ (www.wikipedia.com) አንዳንዶች ዛሬ “የዊክፔዲያ ቀን” እያሉ በሚጠሩት ጥር 15 ቀን በይፋ ስራዉን ጀመረ።<ref>^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.</ref>