ከ«ብጉር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ « '''ብጉር''' ማለት የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከቆዳ ስር በሚገኙ የወዝ እጢዎች በሚመነጭ ቅባት ወይም ወዝ...»
(No difference)

እትም በ19:16, 30 ሴፕቴምበር 2014

ብጉር ማለት የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከቆዳ ስር በሚገኙ የወዝ እጢዎች በሚመነጭ ቅባት ወይም ወዝ እና በሞቱ የቆዳ ህዋሳት በብዛት መከማቸትና በቀዳዳው መደፈን የሚፈጠር እባጭ ነው:: ብጉር ማለት የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከቆዳ ስር በሚገኙ የወዝ እጢዎች በሚመነጭ ቅባት ወይም ወዝ እና በሞቱ የቆዳ ህዋሳት በብዛት መከማቸትና በቀዳዳው መደፈን የሚፈጠር እባጭ ነው:: በርካታ ጥናቶች ጭንቀት ብጉርን ከማባባሱም በላይ የቆዳ ጤንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ይላሉ፡፡

ብጉር በጣም ከተለመዱት የቆዳ ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ዕድሜ ዘርና ጾታ ሳይገድበው ሁሉንም ያጠቃል፡፡ ቆዳችን ላይ ብዙ ጥቃቅን ቀዳዳዎች አሉ፡፡ በነዚህ ቀዳዳዎች ውስጥ ደግሞ ቅባታማ ፈሳሽ የሚያመነጩ ዕጢዎች አሉ፡፡ የቅባታማ ፈሳሽና የቀዳዳዎቹ ጥቅም የሞቱ የቆዳችን ህዋሳትን ለማስወገድ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ ቀዳዳዎች ሲዘጉ ቅባታማ ፈሳሹ በቆዳችን ውስጥ ስለሚጠራቀም ብጉር ይፈጠራል፡፡ የተጠራቀመው ቅባትም ለህዋሳት መራባት ዕድል ስለሚከፍት አንዳነዴ መግል ይይዛል፡፡

የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከ 'ስቤሸስ ግላንድ' (Sebaceous gland) ጋር የተያያዙ ናቸው፡ እነዚህ እጢዎች ሴበም (Sebum) የሚባል ንጥረነገር ሲያመነጩ ንጥረነገሩም በጸጉር መውጫ ቀዳዳ ወደላይ ወደቆዳ የሚወጣ እና ቆዳችን ላይ የሚያርፍ ነው። የብጉር መፈጠር የቆዳ ህዋሳትን ያበዛል። ይህ እባጭ የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎችን ግርግዳ በመግፋት (whiteheads) ነጫጭ የብጉር ሽፍታዎች ሲፈጥር የቀዳዳዎችን ግርግዳ በመጎተት ደግሞ ጥቋቁር የብጉር ሽፍታዎች (blackheads) ቆዳችን ላይ ሊፈጥር ይችላል። ብጉር በብዛት ሊወጣ የሚችልባቸው ቦታዎች፣ ፊት ላይ፣በደረት፣በኣንገት፣በትከሻ ፣እና በጀርባ ላይ ነው::

የብጉር መፈጠሪያ መንስዔዎች

..፩ ከሚገባው በላይ የሆነ የቆዳ ወዝ መመንጨት ሲኖር ..፪ በሞቱ የቆዳ ህዋሳት መፈግፈግ ምክንያት በፀጉር መውጫ ቀዳዳዎች ላይ የሚፈጠር ያልተለመደ ዐይነት የሞቱ የቆዳ ህዋሳት መከማቸት ነው፡

ብጉር ማን ላይ ሊወጣ ይችላል

..• ጉርምስና እድሜ ላይ በደረሱ ልጆች ..• እርጉዝ / ነፍሰጡር ሴቶች ..• እንዲሁም በሌላ አጋጣሚዎች ማንኛውም ሰው ላይ

ብጉርን ማባባስ የሚችሉ ነገሮች

..• ሆርሞኖች ወይም ዕንድሮጅን ..• እንዳንድ ሀክምናዎች ..• ቆዳን በጣም መፈተግ፣ ጥሩ ያልሆኑ የፊት ማጽጃ ሳሙናዎች እና ለኛ የማይስማማ የጺም መቁረጫ መከላከያዎች ..• ቆዳችንን በንጹህና በጥሩ የቆዳ ማጽጃ በመጠቀም፡እንዲሁም በብጉር የተጠቃውን የቆዳ ክፍል በእጅ ባለመነካካት ብጉርን መከላከል እንችላለን፡ ..• ብጉር ያጠቃውን የቆዳ ክፍል በቀን ለሁለት ጊዜ ያህል መታጠብ፡ መታጠብ ብዙ ቅባት እና የሞቱ የቆዳ ህዋሶችን ያስወግዳል በጣም መታጠብ ግን ቆዳችን እንዲፈገፈግ ያደርገዋል። ..• ከባድ ማቆንጃን አለመጠቀም። ..• ከ ዱቄት መኳኳያ በተሻለ የ ቅባት ምርቶችን ይጠቀሙ፡ ምክንያቱም የቆዳ መፈግፈግን ይቀንሳሉ። ..• ወደ መኝታ ክመሄድዎ በፊት የተጠቀሙበትን መኳኳያ ማስወገድ/ መታጠብ፡፡ ..• የመኳኳያ መጠቀሚያዎችን በየጊዜው ማንጻት። ..• ከእስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ከከባድ ስራ በኋላ ሰውነትን መታጠብ:፡

በርካታ ጥናቶች ጭንቀት ብጉርን ከማባባሱም በላይ የቆዳ ጤንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ይላሉ፡፡

ዋቢ ምንጭ