ከ«G» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{ላቲንፊደል}}thumbnail|220px '''G''' / '''g''' በላቲን አልፋቤት ሰባተኛው ፊደል ነው።...»
(No difference)

እትም በ16:13, 21 ጁላይ 2014

የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

G / gላቲን አልፋቤት ሰባተኛው ፊደል ነው።

3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. አስቀድሞ፣ የላቲን አልፋቤት ፯ኛው ፊደል Z ሆኖ ነበር። በአንዳንድ መዝግቦች ዘንድ፣ የሮሜ ኬንሶርና አምባገነን አፒዩስ ክላውዲዩስ ካይኩስ በ320 ዓክልበ. «Z»ን ስላልወደደ ከላቲን ፊደል እንደ ጣለው ይባላል።

እስከዚህም ድረስ፣ ሦስተኛው ፊደል C እንደ ድምጾቹ «ግ» ወይም «ክ» ሊወክል ቻለ። በ230 ዓክልበ. ግድም፣ አስተማሪው ስፑሪዩስ ካርቪሊዩስ ሩጋ የ«ክ» ከ«ግ» ድምጽ ለመለየት፣ «C» ትንሽ በመለውጥ አዲስ ፊደሉን «G» እንደ ፈጠረ ይባላል። ከዚህ ጀምሮ C ለ«ክ» ብቻ፣ G ለ«ግ» ብቻ ይበቃቸው ነበር። በዚህ ወቅት ፊደሎች ደግሞ እንደ ቁጥሮች ስላገለገሉ የሌሎቹን ፊደላት ቁጥሮች ለመጠብቅ አዲሱ ፊደል «G» በቀድሞው «Z» ፋንታ በመተካት በ፯ኛው ሥፍራ ተሰካ። «Z»ም ወደ ላቲኑ አልፋበት በ100 ዓም አካባቢ እንደገና ሲመለስ፣ መጨረሻውን ቦታ ወሰደ።

ከዚህም በኋላ ከ500 ዓ.ም. ግድም ጀምሮ፣ «G» ከአናባቢዎቹ «E»፣ «I» ወይም «Y» ሲቀድም፣ በአሕዛብ ዘንድ እንደ «ጅ» ይሰማ ጀመር። ስለዚህ ከሮማይስጥ በተወለዱት ቋንቋዎች እንደ ጣልኛ ወይም እስፓንኛ GE፣ GI እንደ «ጀ» «ጂ» ይሰማሉ፣ በእንግሊዝኛም ብዙ ጊዜ እንዲሁ ነው። በፈረንሳይኛም GE፣ GI እንደ «ዠ» «ዢ» ይሰማሉ። ሆኖም በነዚህ ልሳናት «G» ከ «A»፣ «O» ወይም «U» በፊት ሲቀድም፣ እንደ «ጋ»፣ «ጎ»፣ «ጉ» ይሰማል።