ከ«ደብረ ብርሃን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

3 bytes added ፣ ከ7 ዓመታት በፊት
no edit summary
በሌላ ገለልተኛ የግምት ትመና ደግሞ ከተማዋ የ፶፯ ሺህ ፯፻፹ ሕዝብ መኖሪያ እንደሆነች ተገምቷል። የከተማዋ አቀማመጥ በ{{coor dm |9|41|N|39|32|E}} ላይ ነው።<ref> Butler, Rhett A., [http://www.mongabay.com/igapo/2005_world_city_populations/Ethiopia.html 2005 population estimates for cities in Ethiopia]</ref>
 
ደብረ ብርሃን ከአዲስ አበባ ፻፴ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደሴበ[[ደሴ]] መስመር ላይ የምትገኝ ስሆን ፱ የአስተዳደር ቀበሌዎችም አሏት። የአየር ንብረቷ ደጋማ ነው። የተቆረቆረችውና ስያሜዋን ያገኘችው ደግሞ በ[[1446|፲፬፻፵፮]] ዓ/ም አካባቢ በ[[ዘርአ ያዕቆብ|ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ]] (፲፬፻፴፬-፲፬፻፷፰) ነበር። ከተማዋ ድሮ የንጉሡ የግራ በአልቴሃት (ግራ በአልቴሃት ከንጉሡ ሦሥት ሚስቶች የአንደኛዋ የክብር ስም ነው) ርስት ነበረች። በ፲፬፻፵ዎቹ መጀመሪያ አጤው ከእንደግብጣን ወጨጫ ተራራ ማለትም ከ[[አዲስ አበባ]] በስተምዕራብ ከነበረው ያባታቸው አጤ ዳዊት መናገሻ ሥፍራ ተነስተው ሲጓዙ በአካባቢው ውበት ስለተደሰቱ የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት። በኋላም ቤተ መንግሥት አሳንፀውና ባለወርቅ ጉልላት የነበረውን የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ቆረቆሯት።
"ተአምረ ማርያም" የተሰኘ የጥንት ድርሳን የከተማዋን ስያሜ ከአንድ ተአምራዊ ሁነት ጋር አያይዞ ይገልፀዋል። በ[[1446|፲፬፻፵፮]] ዓ/ም በክርስትና ሃይማኖት ካህናትና በጥቂት የሃይማኖቱ ተከራካሪዎች መካከል ክርክር ይነሳል። ንጉሡና የካህናቱ አለቆች በተገኙበት አንድ ዕለት በጉባዔ ክርክሩ ተካሄደ። በመጨረሻም «እስጢፋኖሳውያን» በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ተከራካሪዎች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ተጠይቀው አሻፈረን በማለታቸው ከፍተኛ ቅጣት ይደርስባቸዋል። ይህ በሆነ በ፴፰ኛው ቀን በመጋቢት ፲ ቀን 1446|፲፬፻፵፮ ዓ/ም ረዘም ላለ ጊዜ / ምናልባትም ለቀናት/ የቆየ ቦግ ያለ ብርሃን ከሰማይ ይወርዳል። የብርሃኑ መውረድ ለእስጢፋኖሳውያን ስህተተኛነት ለካህናቱ ደግሞ ትክክለኛነት ምስክር ነው በሚል ተተርጉሟል። ስለዚህ ብርሃን መውረድ የንጉሡ ዜና መዋዕልም ያትታል። በዚህ ሳቢያ ንጉሡ የሥፍራውን ስም ደብረ ብርሃን /የብርሃን አምባ/ በማለት ሰይመውታል።
 
3,107

edits