ከ«ኩዱር-ማቡግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «ስዕል:VAM - Korbträgerin.jpg|300px|thumbnail|የኩዱር-ማቡግ ስም ያለበት በሴት ሠራተኛ ቅርጽ የሆነ መሠረት ችንክ...»
 
No edit summary
 
መስመር፡ 2፦
'''ኩዱር-ማቡግ''' (ወይም '''ኩዱር-ማቡክ''') የ[[አሞራውያን]] አለቃ በ[[መስጴጦምያ]] ነበር። አባቱ ሰምቲ-ሺልሃክ ሲሆን የሁለታቸው ስሞች [[ኤላማኛ]] በመሆናቸው [[ኤላም|ኤላማዊ]] እንደ ነበሩ ይታስባል። ሆኖም ኩዱር-ማቡግ እራሱ አሞራዊ ወይም ግማሽ አሞራዊ ነበር የሚሉ መምህሮች አሉ። የኩዱር-ማቡግ ማዕረግ «የማርቱ አባት» ሲሆን፣ ከ1739 ዓክልበ. ጀምሮ «የ[[ያሙትባል]] አባት» ሆነ።
 
በ1745 ዓክልበ. ኩዱር-ማቡግ የ[[ላርሳ]]ን ድካም ንጉሥ [[ሲሊ-አዳድ]]ን ከዙፋኑ አስወግዶ የራሱን ልንልጅ [[ዋራድ-ሲን]] ዘውዱን አጫነው። እንዲሁም ኩዱር-ማቡግ [[ካዛሉ]]ን፣ [[ሙቲባል]]ንና [[ኤሽኑና]]ን እንዳሸነፈ ይመስላል። ሌላውም ልጅ [[ሪም-ሲን]] ወንድሙን በላርሳ ዙፋን በ1734 ዓክልበ. ተከተለ። የኩዱር-ማቡግ ሴት ልጅ ኤን-አነዱ ደግሞ የ[[ኡር]] መቅደስ ከፍተኛ ሴት ካህን ሆነች። ሌላም ወንድ ሊጅ ሲን-ሙባሊት ተባለ። እነዚህ ልጆች ስሞች ሁሉ [[አካድኛ]] እንጂ ኤላምኛ አይደሉም። ሌላ ሴት ልጁ ማንዚ-ዋርታሽ ግን ኤላምኛ ስም አላት።
 
ኩዱር-ማቡግ ምናልባት 1730 ዓክልበ. አካባቢ ዓረፈ።