ከ«አማራ (ክልል)» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 8፦
[[ምዕ/ጎጃም ዞን]]ም በዚሁ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ ቡሬ ወምበርማ ወረዳ፡ ሰከላ፡ ይልማና ደንሳ፡ [[ደምበጫ]]ና [[ዳሞት]] ወረዳዎችን ይገኙበታል። ቡሬ ወረዳ የንግድ ማኣከል ስትሆን [[ወለጋ]]ን ([[ነቀምት]]ን)፡ [[አዲስ አበባ]]ን አና [[ባህር ዳር]]ን ታገናኛለች። በወረዳዋ ዉስጥ ሁሉም አዝዕርቶች የሚመረቱ ቢሆንም በዋናነት [[በርበሬ]]፡ [[ጤፍ]]፡ [[በቆሎ]]፡ በብዛት ይመረታሉ። ቡሬ ወረዳ አንድ ግብርና ማሰልጠኛ፡ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፡ 1 ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ፡ 1 ፕሪፓራቶሪ አና 3 አንደኛና መለስተኛ ት/ቤቶች ይገኙባታል። የማዕድን ዉሃ ፋብሪካና ሌሎች የግብርና ማቀነባበሪያዎችም ይገኛሉ። ለግብርና ኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ የአየር ንብረትና መሬት ያላት ወረዳ ስትሆን ባለሃብቶች በዚህ አካባቢ ቢሰማሩ ዕራሳቸዉን ጠቅመቅው ህብረተሰቡን መጥቀም ይችላሉ።
 
==የተፈጥሮ ሀብት==
በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማና ተራራማ ስፍራዎች ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ [[ቀይ ቀበሮ]]፣ [[ዋልያ]]፣ [[ጭላዳ ዝንጀሮ]] እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ [[ዝሆን]] [[አንበሳ]]ና [[ነብር]]፣ [[ሰጐን]]ና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል፡፡
 
መስመር፡ 16፦
ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የ[[ዓባይ]]፣ የ[[ተከዜ]] እና የ[[አዋሽ ወንዝ|አዋሽ]] ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው።
 
==ምጣኔ ሀብት==
በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ።
 
==የጎብኚዎች መስሕብ==
በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች፣ የ[[ላሊበላ]] አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው። ለምሳሌ ከሚጠቀሱት መኃል ፦ አደል ሚካኤል፡ ይስር ፏፏቴ፡ ባንጃ ተራራው ወዘተ...
 
==ዋቢ ምንጭ==
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ድረ-ገጽ፤ "የክልሉ አጠቃላይ ገጽታ" (accessed 21 Dec 2012)
http://www.amharainfo.gov.et/index.html/index.php?option=com_content&view=article&id=61%3A2011-02-10-05-51-55&catid=7%3Aoverview-of-the-region&Itemid=29&lang=en