ከ«አማራ (ክልል)» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
የ108.18.52.246ን ለውጦች ወደ Codex Sinaiticus እትም መለሰ።
መስመር፡ 13፦
የክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በ[[ሰሜን ሸዋ]] የኦፓል ማዕድን፣ በ[[ሰሜን ጐንደር]]፣ በ[[ጭልጋ]]ና በ[[ደቡብ ወሎ]] በ[[አምባሰል ወረዳ]] የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።
 
=የውሐ=የውሀ ሀብት==
ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የ[[ዓባይ]]፣ የ[[ተከዜ]] እና የ[[አዋሽ ወንዝ|አዋሽ]] ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው።