ከ«መለስ ዜናዊ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ገጹን «መለስ ዜናዊ» ፈታ።: semi-protected since 2008, opening now to all editors but can be re-locked if problems follow
መስመር፡ 43፦
ጠ/ሚ መለስ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ብሔረሰብ እንዲገነጠል የሚያስችለውን አንቀጽ በሕገ መንግስታቸው በማካተታቸው በተለይ በምሁራን ዘንድ የከረረ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ይማር የተሰኘው ፖሊሲያችውም በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬና መከፋፈልን በመፍጠሩ በሀገርና ከሀገር ውጭ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ተካይዶባቸዋል።
 
በ1997 አጋማሽ ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ከተለያዩ የፖለቲካ ህቡዕየፖለ ፓርቲዎች የተውጣጣ [[ቅንጅት]] የተሰኘ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተወዳደረ። በውጤቱም የዓለም ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ከመቶ 97 እጁ መራጭ የተቃዋሚውን ፓርቲ ቅንጅትን መረጠ። በውጤቱ የተደናገጠው የአቶ መለስ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ቁጥጥር ስር አዞረ። የአዲስ አበባ ምክር ቤትንም በ[[ኦሮሚያ]] መስተዳደር ስር እንዲተዳደር አዲስ ድንጋጌ አወጣ።
 
ይሁን እንጂ ብዙም ገለልተኛ ታዛቢ በሌለበት ከአዲስ አበባ ውጪ [[ኢሕአዴግ]] 90 በመቶ ማሸነፉ ስለታወጀ ተቃዋሚዎች አድልዎ ተደርጎብናልና ምርጫው እንደገና ይጣራ ብለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በማስገባታቸው ማጣሪያ ተካሄደ። ተቃዎሚዎች በጠቅላላው የምርጫ ውጤት ባለመስማማታቸው ያሸነፉበትን የፓርላማ ወንበር ባለመቀበል የገዢው ፓርቲ በበላይነት ከተቆጣጠረው ፓርላማ ራሳቸውን አገለሉ።
 
[[ሚሥስ አና ጎሜዝ]] የተባሉ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ምርጫው አድልዎና ጫና እንደነበረበት ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸውን ተናገሩ። አብዛኛዎቹ ታዛቢዎች ([[አፍሪካ ሕብረት]] አና የ[[ጂሚ ካርተር]]ማእከል) ምርጫው በኢትዮጲያ ከተካሄዱ ምርጫዎች በጣም የተሻለ መሆኑን መሰከሩ። በሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ደጋፊዎች በዋና ዋና ከተማዎች በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ በቁጣ በሚገልጹበት ጊዜ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ በፖሊስ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱን አጥቶአል። የአቶ መለስ መንግስት አብዛኛዎችን በህዝብ የተመረጡ የ[[ቅንጅት]] ፓርቲ አባላትንና በሺህ የሚቆጠሩ አባላትን ባገር ክህደት አና መንግስትን ለመገልበጥ በመሞከር ከሰሳቸው። 2 ዓመት በፈጀ የፍርድ ሂደትም ፍርድ ቤቱ የቅንጅት መሪዎችን አገርን በመክዳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አገኛቸው ። ይሁን እንጂ ሁሉም የ [[ቅንጅት]] መሪዎችና አብዛኛው ደጋፊ አባላት ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር ነጻ ወጡ።
 
{{Template:EthiopianPMs}}