ከ«ዳግማዊ ምኒልክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 49፦
==የምርኮ እና ስደት ዘመናት==
 
[[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ለሳቸው ያልገቡ ብዙ የ[[ሸዋ]] መኳንንት ስለነበሩ ይወስዱብኛል በሚል ፍርሀት ምኒልክን በሰንሰለት አሳሰሯቸው። ንጉሠ ነገሥቱ ግን ምኒልክ በመታሠሩ ሲያለቅስ እንዳደር ሲሰሙ አዝነው ሰንሰለቱን እንዲፈቱላቸው አዘዙ። በ[[ጥር]] ወር [[1849|፲፰፻፵፱]] ዓ/ም [[መቅደላ]] ገብተው በቁም እሥር ይቀመጡ እንጂ ከቴዎድሮስ ልጅ ከመሸሻ ጋር አብረው አደጉ። ወዲያውም የ[[ደጃዝማች]]ነት ማዕረግ ተሹመው በጥር ወር [[1856|፲፰፻፶፮]] ዓ.ም የዓፄ ቴዎድሮስን ልጅ ወይዘሮ አልጣሽን አገቡ። በዚህ ሁኔታ እድሜያቸው ፳፪ ዓመታቸው ድረስ ለ አሥር ዓመታት ዓፄ ቴዎድሮስ ግቢ ኖሩ።
 
[[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ምኒልክን እንደልጃቸው ያዩዋቸው እንደነበረና በታላቅ ጥንቃቄም እንዳስተማሯቸው እንደ [[ኢጣልያ]]ዊው ጉሌልሞ ማሳያ፤ ዓለቃ ወልደ ማርያም እና ዓለቃ ገብረ ሥላሴ የመሳሰሉ መስክረዋል። ምኒልክም ቴዎድሮስን እንደአባት ይወዷቸው እንደነበር ይገለጻል። በኋለኛው ጊዜ [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] መሞታቸውን ሲሰሙ ንጉሥ ምኒልክ በጣም ማዘናቸውንና የመንግሥት ሐዘንም ማወጃቸው ተዘግቧል።