ከ«ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

3,438 bytes removed ፣ ከ6 ዓመታት በፊት
 
ስለዚህ ለመታገሥ የማይችል ሲሆንባት ጊዜ በግብፅ አገር አንድ ዐይነት በተናከሰ ጊዜ ሕመሙ የማይሰማ መርዛም እባብ ስላለ ክሌዎፓትራ ከንደዚህ ያለ መርዛም እባብ አንዱን አሲዛ አስመጥታ ሰውነቷን አስነከሰች። ትንሽ ቆይታ ሁለመናዋ ደነዘዘ አበጠ ወዲያው ልቡዋ መምታቱን አቆመ። ውበት የነበራት ክፋዩቱ የግብፅ ንግሥት ክሌዎፓትራ እንደዚህ ሆና ፴ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሞተች።
 
=== ተከታይ ታሪክ ===
ከንግሥት ክሌዎፓትራ ሞት በኋላ ግብፅ ለሮማ መንግሥት ተገዛና እስከ ዘመነ ክርስትና ፮፻፵ ዓመት ድረስ የምሥራቅ መንግሥት እየተባለ ለሮማ እንደ ተገዛ ቆየ። ከዚህ በኋላ ሳራሲኖች ድል አደረጉትና እስከ ፮፻ ዓመት ቆየ።
 
የሳራሲን ገዦች ያሠለጠኗቸው [[ማምሉክ|ማምሉኮች]] የተባሉት የገዛ ዘበኞቻቸው ሳራሲኖችን ከዙፋናቸው ዘርጥጠው አወረዷቸው። ቱርክ መጥቶ ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ማምሉኮች ግብፅን እስከ ፲፯፻፱ ገዝተዋል። ቱርኮችም ግብፅን እስከ ፲፯፻፺፰ ዓመት ገዝተዋል። ከዚህ በኋላ [[ናፖሊዮን ቦናፓርቲ]] አርባ ሺህ የሚሆን የጦር ሠራዊት ከ[[ፈረንሳይ]] አገር አምጥቶ፤ ግብፅን ወረረ።
 
ቱርኮችም ግብፅን ከያዙ ወዲህ ማምሉክ የተባለውን ጭፍራ ወደ ሥራቸው አግብተው ጠብቀውት ነበርና እነዚህ ተስፋ እስኪቆርጡ ድረስ ተከላከሉ። ጦርነቱን የሚዋጉበት ስፍራ በፒራሚዱ አጠገብ ነበር። በዚያ ሲዋጉ ሳሉ እኩሌቶቹ እዚያው ታረዱ። ሌሎቹም እየዘለሉ ወደ ነጭ ዐባይ ወንዝ ባሕር ሰጠሙ። ከዚህ ጦርነነት በኋላ ናፖሊዮን ቶሎ ብሎ ወዲያው ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ እንጂ በዚህ አልዘገየም። ሲሄድም ጀኔራል ክሌበር የተባለውን ለፈረንሳይ ጦር ጠቅላይ አድርጎት ሄደ።
 
ጀኔራል ክሌበር ጀግና ሰው ነበር። ዳሩ ግን ጨካኝ ነበርና ጨካኝነቱ ሕይወቱን እስከ ማጣት አደረሰው።
 
ይኸው ጨካኙ ጀኔራል አንድ ቀን ሼህ ሳዳ የሚባል አንድ ሽማግሌ እስላም አገኘና ውስጥ እግሩን በከዘራ አስደበደበው። ወዲያው ትንሽ እንደ ቆየ ጀኔራሉ ወደ መስጊድ ገብቶ ሳለ አንድ የተናደደ እስላም ገሠገሠና በጩቤ ቢሽጥበት ያን ጊዜውኑ ሞተ።
 
በ፲፰፻፩ ዓመት [[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] ፈርንሳዮችን ከግብፅ ለማስወጣት ከብዙ ጦር ጋራ ሰር [[ራልፍ አቤሮክሮምቢ]]ን ሰደደው። ጀኔራል መኑ የፈረንሳይ ኮማንደር ነበር። [[አቡኬር]] ላይ ተዋጉና ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢ ድል አደረገው። ዳሩ ግን እርሱም ራሱ ክፉኛ ቆስሎ ነበር።
 
በዚያው ዓመት የፈርንሳይ ጦር ተሸነፈና ከግብፅ ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ። ዳሩ ግን ባላገሮቹ ከፊተኞቹ ገዢዎቻቸው ከቱርኮች ይልቅ የፈረንሳይ ጀኔራል ቅን ፍርድ እየፈረደ በመልካም አገዛዝ በደንብና በሕግ ይገዛቸው ነበርና በመሄዱ እጅግ አዝነው ተላቀሱ።
 
የዛሬው የግብፅ ዋና ከተማ ትልቁ ካይሮ ነው። ቀድሞ ከነበረው ይልቅ የዛሬው በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ፫፻ ሺህ ሰዎች ይኖሩበታል።
 
== ባህል ==
Anonymous user