ከ«ጥንታዊ ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 11፦
 
የሃይሮግሊፍ ቅርሶችና መዝገቦች ለማንበብ ችሎታው አሁን ስላለ፣ ሜኒስ ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ በጥቂት መጠን ተገልጾአል። መጀመርያው ሥርወ መንግሥታት (፩ኛው እስከ ፮ኛው ድረስ) የቀድሞ ዘመን መንግሥት ይባላሉ። በ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ሰባአዊ መስዋዕት በሰፊ ይደረግ ነበርና ከፈርዖኖቹ ጋራ ብዙ ሎሌዎች አብረው ይቀበሩ ነበር። የሔሩ ወገን በሴት ወገን ላይ ይበረታ ነበር። በ፪ኛው ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች መቃብር ከተማ ከላይኛ ግብጽ ወደ ታችኛ ግብጽ (ስሜኑ) ተዛወረ። በኋለኛ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን የሴት ወገን ወኪል ፈርዖን [[ፐሪብሰን]] ተነሣና ያንጊዜ ትግሎች እንደ በዙ ይመስላል። በ፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ የሔሩ ወገን ለሥልጣን ተመልሶ፣ [[ነጨሪኸት]] የተባለው ፈርዖን የመጀመርያውን [[ሀረም]] (ፒራሚድ) አሠራ። ከርሱም በኋላ የተነሡት ታላላቅ ፈርዖኖች በ[[ጊዛ ሜዳ]] ላይ ፒራሚዶቻቸውን እንዲሁም [[የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ]]ን ሠሩ። በ፬ኛውም ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች ዝሙት የገዛ እኅቶቻቸውን እስከሚያግቡ ድረስ ደረሰ። በ፭ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖኖች በሀረሞቻቸው ውስጥ [[የሀረም ጽሕፈቶች]] ያስቀረጹ ጀመር፤ እነኚህ ጽሕፈቶች የሔሩ ተከታዮች ወገን (ወይም «ደቂቃ ሔሩ») በሴት ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸሙትን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት ይመሰክራሉ። ይህም አስጨናቂ ሁኔታ በ፮ኛው ሥርወ መንግሥት እየተቀጠለ ፈርዖኖቹ ዓለማቸውን ሁሉ ከነጎረቤቶቻቸውም ጋር በጽናት ይገዙ ነበር።
 
በ[[ኤብላ]]፣ [[ሶርያ]] የ፮ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን [[1 ፔፒ]] ቅርስ በፍርስራሹ ስለተገነ፣ አብዛኛው ሊቃውንት ፔፒ በኤብላ ዘመን በ2300 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ገመቱ። ስለዚህ የቀድሞ ዘመን መጨረሻ በፍጹም ተስተዋል። ነገር ግን ይህ በጥንታዊ ቅርሶች ክምችት መካከል ስለተገኘ ዕድሜስ በዚያ ሊታወቅ አይችልም።<ref>Michael C. Astour, Eblaitica 4, p. 60.</ref> የቀድሞ ዘመናት ቅርሶች የተገኙባቸው ሥፍራዎች ኤብላና [[ጌባል]] በዘመናቸው የቀድሞ ዘመን ቅርሶች ጥናት መኃሎች ስለ ነበሩ እንደ ሙዚየም ያህል ቦታዎች ነበሩባቸው።
 
በተጨማሪ ለቀድሞ ነገሥታት ዘመኖች ዋና ምንጭ የሆነው ''[[ንጉሣዊ ዜና መዋዕል]]'' (ወይም «የፓሌርሞ ድንጋይ») በክፍሎች ሲካፈል፣ በየሁለቱ ክፍሎች የላም ቁጠራ ሰለተቆጠረ፣ እያንዳንዱ ክፍል አንድ ዓመት ሳይሆን አይቀርም የከብትም ቁጠራ የተደረገው በየ፪ ዓመት ነበር ብለው ገመቱ። ሆኖም በሠንጠረዡ እያንዳንዱ ክፍል ፮ ወር ከሆነ፣ የከብት ቁጠራ በየዓመቱ ይደረግ ነበር። ስለዚህ በብዙ መምህሮች ግምት የብዙ ፈርዖኖች ዘመን በ፪ ዕጥፍ ተረዘመ።
 
==መጀመርያው መካከለኛ ዘመን==