ከ«አማር-ሲን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «File:P1150892_Louvre_figurine-clou-Ur_AO3142_rwk.jpg|280px|thumb|An architectural foundation-nail figurine depicting king Amar-Sin himself carrying the builder...» |
(No difference)
|
እትም በ19:44, 23 ማርች 2014
አማር-ሲን ከ1918 እስከ 1909 ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአባቱ የሹልጊ ተከታይ ነበር። ቀድሞ ስሙ እንደ ቡር-ሲን በሊቃውንቱ ይታነብ ነበር፤ አሁን ግን አጠራሩ «አማር-ሲን» ትክክል እንደ ሆነ ይታመናል።
ለ፱ኝ ዓመቶቹ ሁላቸው በስም ይታወቃሉ። ዘመቻዎች በኡርቢሉምና በተለያዩ ቦታዎች (ሻሽሩም፣ ሹሩድሁም፣ ቢቱም-ራቢዩም፣ ጃብሩና ሑሕኑሪ) ላይ ይመዘገባሉ።[1] በተረፈ አማር-ሲን በኤላማዊ ነገሥታት እንደ ማርሐሺ ንጉሥ አርዊሉክፒ እንደ ዘመተ ይታወቃል። የዑር መንግሥት በአማር-ሲን ዘመን እስከ ስሜናዊ ግዛቶች እስከ ሉሉቢና ሐማዚ ድረስ ተዘረጋ። ደግሞ ዓመጽ በአሹር አሸንፎ አካዳዊ ሻካናካ (ከንቲባ) ዛሪቁም በአሦር ላይ ሾመ።[2]
አማር-ሲን የሱመር ጥንታዊ ሥፍራዎች በተለይ በኤሪዱ የነበረው ትያላው ግንብ ለማሳደስ ሠራ።[3]
የባቢሎናዊ «ዋይድነር ዜና መዋዐል የተባለው ሰነድ እንዲህ ይላል፦ «የሹልጊ ልጅ አማር-ሲን የአኪቱ በዓል በሬና በጎች መሥዋዕት ቀየረ። በበሬ ውግያ እንዲሞት ተነበየ፤ ሆንቦም ከጫማው መንከስ [ጊንጥ?] ሞተ።»
የአማር-ሲን ልጅ (ወይም ወንድም?) ሹ-ሲን በዑር ዙፋን ተከተለው።
ቀዳሚው ሹልጊ |
የሱመር ነጉሥ 1918-1909 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሹ-ሲን |
- ^ Year-names for Amar-Sin
- ^ Potts, The Archaeology of Elam, p. 132.
- ^ Karen Frieden