ከ«ራስ መኮንን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 8፦
በ[[1898|፲፰፻፺፰]] ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ [[አዲስ አበባ]] ለመሄድ [[ጥር 4|ጥር ፬]] ቀን ከከተማቸው ከ[[ሐረር]] ተነሱ። [[ጥር 9|ጥር ፱]]ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የ[[ጥምቀት]]ን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ [[መጋቢት 13|መጋቢት ፲፫]] ቀን [[1898|፲፰፻፺፰]] ዓ.ም [[ቁልቢ]] ላይ አርፈው [[ሐረር]] ላይ እሳቸው በተከሉት በ[[ቅዱስ ሚካኤል]] [[ቤተ ክርስቲያን]] ተቀበሩ።<references/> ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው [[አዲስ አበባ]] እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ [[ሰኞ]] [[ሚያዝያ 22|ሚያዝያ ፳፪]] ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የ[[ክርስቲያን]] የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም [[ማክሰኞ]] የ[[ጊዮርጊስ]] ዕለት [[ሚያዚያ 23|ሚያዝያ ፳፫]]ቀን [[1898|፲፰፻፺፰]] ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው። ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ፤-
 
:'''«ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው፤ '''
:'''መኮንን አይደለም ድኃ ነው የሞተው»'''
 
== ዋቢ መጻሕፍት ==