ከ«መጽሐፍ ቅዱስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 7፦
 
በ[[ካቶሊክ ቤተክርስቲያን]] እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በ[[ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን]] እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።
 
አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። [[ግኖስቲክ]] የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቶቹን ከነሄኖክና ኩፋሌ ያንብቡ ነበር። የ[[አይሁድ]] [[ሰንሄድሪን]] ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ በተለይም ረቢ [[አኪቫ በን ዮሴፍ]] እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። [[መሊቶ ዘሳርዲስ]] የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ [[ኢየሩሳሌም]] መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቶቹ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በ[[ሮሜ መንግሥት]] ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች [[ቀኖና]] በ[[ንቅያ ጉባኤ]] ([[317]] ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና።
 
== የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ባህርያት ==