ከ«ውክፔዲያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 47፦
ስለሆነም ምንም እንኳን ዉክፔዲያ በብዙ ረገድ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም የተለያዩ መጣጥፎች የተለያየ የሀሳብ ጥልቀትና ጥራት ሊኖራቸዉ ስለሚችል ዊክፔዲያን እንደ አንድ የምርምር ማጣቀሻነት ከመጠቀም ጎን ለጎን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ይመከራል። በዚህ ረገድ መረጃ በመስጠት ተጠቃሚን የሚያግዙ ገፆች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ከነዚህም መካክል የማመላከቻና የመረጃ ገጽንና ስለ ዉክፔዲያ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭነት የተደረጉ የሶስተኛ ወገን ጥናቶችን መመልከት ይቻላል።
 
Hoi Piet
=== ዊክፔዲያ ከሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነፃጸር ===
ዊክፔዲያ ቀደም ሲል በስፋት ይዉሉ ከነበሩ የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች<ref>^ "Encyclopaedia Britannica and Nature: a response". Retrieved July 13, 2010.</ref> ጋር ሲነፃጸር ከፈተኛና የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለዉ። በመጀመሪያ ደረጃም አነስተኛ የህትመትና የማስፋፋት ወጭና የሚጠይቅ መሆኑና ዝቀተኛ የሆነ የጎንዮሽ አካባቢያዊ ተፅኖች ያሉት መሀኑን ማንሳት ይቻላል። በሌላ በኩል ምንም አይነት የህትመት ስራ የማይፈለግ በመሆኑ ኮምፒዉተሮች የራሳቸዉ የሆነ አካባቢያዊ ተጽኖ ይኖራቸዋል።
 
በተጨማሪም ሁሉንም አይነት መግለጫዎችን በአንድ ገጽ አካቶ ከመያዝ ይልቅ እርስበርስ የሚዛመዱና በሌሎች የተለያዩ ገጾች የተብራሩ ጉዳዮችን ከአጫጭር ማጠቃለያዎች ጋር አጣምሮ በማቀረብ በቀላሉ መረጃን ለማግኘት ይረዳል። በመጨረሻም እንዴ ሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች የተወሰነ የአርትኦትና የማሻሻያ ጊዜን የማይጠይቅ በመሆኑ፣ ዉክፔዲያ ከሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነጻጸር አጭር የአርትኦት ጊዜን የሚጠይቅና በማንኛዉም ጊዜና ሰአት መሻሻሎችን በማደረግ መጣጠፎች ወቅታዊና ጊዜዉን የተበቀ መረጃን ይዘዉ እንዲቀጥሉ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራርን ይፈቅዳል።
== ማጣቀሻዎች ==
<references/>