ከ«ውክፔዲያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አንድ ለውጥ ከ62.155.161.237 (ውይይት) ገለበጠ
መስመር፡ 11፦
በሌላ በኩል፣ ዉክፔዲያ አንድ ሰዉ ካለዉ የሙያ ችሎታ ይልቅ ለሚያበረክተዉ አስተዋፆ ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል፣ ባህልና መነሻ (ዳራ) የሚገኝ ማንኛዉም ሰዉ የዉክፔዲያ አስገዳጅ ፖሊሲዎችን አሟልቶ እስከተገኘ ድረስ፣ ዉክፔዲያ ላይ የፈለገዉን መጣጥፍ እንዳንድስ የመጨመር አሊያም ማንኛዉም ዉክፔዲያ ላይ የሚገኝ ሌላ ጽሑፍ፣ ማጣቀሻና ምስል የማየት የማሻሻልና የማረም አንዳደም ሙሉ ለሙሉ የመለዎጥና ፈቃድ አለዉ። በመሆኑም ዉክፔዲያ በተለያዩ አስተዋጾ አድራጎዎች በየጊዜዉ ማሻሻያ የሚደረግበት እንደመሆኑ መጠን፣ አድስ ከሚካተቱት መጣጥፎች ይልቅ ቀደም ሲል በድረ ገጹ የተካተቱ መጣጥፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታረሙና እየተሻሻሉ የሚሄዱ በመሆናቸዉ የተሻለ የሃሳብ ጥራት፣ የመረጃ ሚዛናዊነትና ሙሉዕነት እንደሚኖራቸዉ ይታመናል።
 
==yfdveduyvfduye
== የዊክፔዲያ አመሰራረት ==
ዊክፔዲያ ነፃ ኦላይን መዝገበ-ዕዉቀትን (free encyclopedia) ለመፍጠር አላማ አድርጎ የተመሰረተና ቀደም ሲል [[ኑፔዲያ]] (Nupedia) በመባል የሚታወቅ ፕሮጀክት ዉጤት ነዉ። ኑፔዲያ ምንም እንኳን የተሻሻለ የዕርስ-በርዕስ መገማገሚያ (peer review) መንገዶችን አካቶ የያዘና ሙያዊ ብቃት ያላቸዉ መጣጥፍ አቅራቢዎችን የሚጠይቅ ፕሮጀክት የነበረ ቢሆንም መጣጥፎችን አትሞ ለማዉጣት ረጅም ጊዜን ይጠይቅ ነበር። በመሆኑም ይንንም ችግር ለመቅረፍ፣ በ[[2000 እ.ኤ.አ.]] የኑፔዲያ መስራቹ [[ጂሚ ዌልስ]]ና በዚሁ ፕሮጀክት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ [[ላሪ ሳንገር]]<ref>Mike Miliard (March 1, 2008). "Wikipediots: Who Are These Devoted, Even Obsessive Contributors to Wikipedia?". Salt Lake City Weekly. Retrieved December 18, 2008.</ref> የተባለ ሌላ ግለሰብ ኑፔዲያን እንደት ማሻሻልና ሌሎች ተጨማሪ ገፅታዎችን አካቶ የሚይዝ ፕሮጀከት ማደረግ እንሚቻል የጋራ ዉይይት አደረጉ።<ref>How I started Wikipedia, presentation by Larry Sanger</ref> በዉይይታቸዉም ወቅት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸዉ አብዛሐኛዎቹ ምንጮች አንድ የዊኪ ድረ-ገጽ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸዉን አስተዋፆ ማበረከት የሚችሉበት መዳረሻ ተደርጎ ድዛይን ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱዋቸዉ። በዚህም መሰረት ማንኛዉም ሰዉ የራሱን አድስ አስተዋፆ ማበርከትና ብሎም ሌሎች የቀረቡ መረጃዎችን ማስተካክልና ማረም እንዲያስችል ተደርጎ ዲዛይን የተተደረገዉ የመጀመሪያዉ የኑፔዲያ የዊኪ ገፅ እ.ኤ.አ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. አየር ላይ ዋለ።<ref>^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.</ref>
 
ነገር ግን ሌሎች የኑፔዲያ ፕሮጀክት አካል የነበሩ አርታኢዎችና ሀያሲዎች በኑፔዲያ ፕሮጀክት ላይ የተደረገዉን የማሻሻያ ለዉጥ በተለየም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸዉን አስተዋሶ ማበርከት የሚያስችልን ድረ ገፅ(ዊኪ) ቅርፅ እዲይዝ ተደርጎ መሻሻሉን በመቃዎማቸዉ፣ የተሻሻለዉ የኑፔዲያ ፕሮጀክት አድስ የስያሜ ለዉጥ በማድረግና “ዊክፔዲያ” በመባል በራሱ አድራሻ (www.wikipedia.com) አንዳንዶች ዛሬ “የዊክፔዲያ ቀን” እያሉ በሚጠሩት ጥር 15 ቀን በይፋ ስራዉን ጀመረ።<ref>^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.</ref>
 
ለዊክፔዲያ [[ሳንዲዬጎ]] የሚገኘዉንና የመጀመሪያዉ የድረ-ገፁ መቀመጫ በመሆን ያገለገለዉን [[ሰርቨር ኮምፒዉተር]]ና የመረጃ ማስተላለፊያ መስመሩን (bandwidth) በርዳታ የለገሰዉ ጂሚ ዌልስ ነበር። በተጨማሪም በራሱ በጂሚ ዌልስ እና በሌሎች ሁለት ጓደኞቹ የተቋቋመዉና በአነስተኛ የኢንተርኔት የማስታዎቂያ ስራዎች ላይ የተሰማራ [[ቦሚስ]] (bomis) የሚባል ድርጅት ሰራተኞች የነበሩና ባሁኑ ጊዜም እየሰሩ የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችም የራሳቸዉን አስተዋፆ ለዊክፔዲያ አበርክተዋል። በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት፣ የቦሚስ ተባባሪ መስራችና በአሁኑ ጊዜ የድርጂቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገለ የሚገኘዉ ቲም ሸልና ፕሮገራመሩ ጃሰን ሪቺ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ዊክፔዲያ አሁን ወደ ሚታወቅበት www.wikipedia.org የአድራሻ ለዉጥ ያደረገዉ ለትርፍ የማይንቀሳቀሰዉና የራሱ የዊክፔዲያ እህት ኩባኒያ የሆነዉ “ዊክፔዲያ ፋዉንደሽን” ከተቋቋመ በሗላ ነበር።<ref>Jonathan Sidener (December 6, 2004). "Everyone's Encyclopedia". The San Diego Union-Tribune. Retrieved October 15, 2006.</ref>
 
ዊክፔዲያ ምንም እንኳ መጀመሪያ የተመሰረተዉ እንግሊዘኛ ቋንቋን መሰረት አድርጎ ቢሆንም እ.ኤ.አ ከግንቦት 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ሌሎች አዳድስ ቋንቋዎችን በማካተት የበርካታ ቋንቋዎች መዳረሻ ለመሆን ችሏል። ከነዚህም መካከል [[ካታልኛ]]፣ [[ቻይንኛ]]፣ [[ጀርመንኛ]]፣ [[ሞስኮብኛ]]፣ [[ፈረንሳይኛ]]፣ [[ዕብራይስጥ]]፣ [[ጣሊያንኛ]]፣ [[ጃፓንኛ]]፣ [[ፖርቹጋልኛ]]ና [[ስፓንሽኛ]] በግንባር ቀደምትነት ዊክፔድያን የተቀላቀሉ ቋንቋዎች ሲሆኑ፣ [[አረብኛ]]፣ [[ሀንጋሪኛ]]፣ [[ፖሎንኛ]]ና [[ሆላንድኛ]] ከላይ የተጠቀሱትን ቋንቋዎች በቅርብ እርቀት ተከትለዉ የተቀላቀሉ ሌሎች ቋንቋዎች ናቸዉ። በሌላ በኩል በጥር [[2012 እ.ኤ.አ.]] በተደረገ ጥናት ዊክፔድያ ከ31 ሚሊዎን በላይ በሚሆኑ የተመዘገቡ የዊኪፒዲያ አስተዋፆ አድራጎዎችና በመላዉ አለም በሚገኙ ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ ያልተመዘገቡ (የማይታወቁ) አስተዋፆ አድራጎዎች በ283 ቋንቋዎች ከ20 ሚሊዎን በላይ የሚሆኑና ማንምሰዉ በነፃ ሊገልባቸዉ የሚችሉ መጣጥፎችን አካቶ መያዙ ተረጋግጧል። በተጨማሪም ከጠቅላላዉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዉስጥ 14.5% ዊክፔዲያን እንደሚጎበኙ ተረጋግጧል።<ref>Size of Wikipedia</ref>
 
== የንግድ ምልክትና የኮፒራይት ህግ ==