ከ«ጀርመን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 22፦
 
==ባህልና ጠቅላላ መረጃ==
ጀርመን አንድ ይፋዊ ቋንቋ ብቻ አለው እርሱም [[ጀርመንኛ]] ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የጀርመንየጀርመንኛ ቀበሌኞች በአገሩ ይገኛሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ጀርመን «የገጣሚዎችና የአሳቢዎች አገር» በመባል ታውቋል። በዓመታት ላይ በ[[ሥነ ጽሑፍ]]፣ በ[[ሥነ ጥበብ]]፣ በ[[ፍልስፍና]]፣ በ[[ሙዚቃ]]፣ በ[[ሲኒማ]]፣ እና በ[[ሳይንስ]] ዘርፎች በርካታ አስተዋጽኦች በማቅረባቸው ጀርመናውያን በዓለም ዝነኛነት አገኝተዋል፤ እንዲሁም [[መኪና]] የሚባለውን ፈጠራ በማስለማት ፈር ቀዳጅ ሆኑ። ጀርመን ደግም ስለ [[ቋሊማ]]ና [[ቢራ]]ዎች ልዩነት ብዛት የገነነ ሆኗል። [[እግር ኳስ]] በጀርመን ከሁሉ የተወደደው [[እስፖርት]] ነው።
 
የ[[ራይን ወንዝ]] አቅራቢያ በጥንት ከሁሉ በፊት የተሰፈረው ሲሆን እዚያ አንዳንድ ጥንታዊ [[የሮሜ መንግሥት]] ድልድይ፣ አምባ፣ ወይም ፍርስራሽ ሊታይ ይችላል። የጀርመን ሕዝብ በብዛት [[ክርስትና|ክርስቲያኖች]] ናቸው፤ በስደትም ወደ አገራቸው ለደረሱት ሰዎች በጠቅላላው ሰላምታ ሰጪዎች ናቸው። [[የበርሊን ግድግዳ]] በፈረሰበትና «[[የቅዝቃዛ ጦርነት]]» በጨረሰበት ወቅት [[የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ]] ተከሠተ። በዚያ ሰዓት የቀድሞ አገራት [[ምሥራቅ ጀርመን]]ና [[ምዕራብ ጀርመን]] አብረው የአሁኑን ጀርመን መንግሥት ፈጠሩ።