ከ«መልከ ጼዴቅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot: Replacing category ሰዎች with የብሉይ ኪዳን ሰዎች
No edit summary
መስመር፡ 23፦
ከዚህ በላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለ መልከ ጼዴቅ የተለያዩ ትምህርቶችና ታሪኮች አሉ።
 
*''[[ኪታብ አል-ማጋል]]'' በ[[ቅሌምንጦስ ሥነ ጽሑፍ]] ውስጥ ይመደባል። በዚህ ጹሑፍ ዘንድ፣ [[ሰብአ ሠገል]] ብራናውን ለክርስቶስ በሕጻንነቱ እንደ ስጦታ ሰጡት፣ እሱም ለ[[ጴጥሮስ]]፣ ጴጥሮስም ለተከታዩ ለሮሜ 2ኛው [[ፓፓ]] ለ[[ቅሌምንጦስ]] ያቀረበው ታሪክ ነው። በዚህ መሠረት፣ የመልከ ጼዴቅ አባት የ[[አርፋክስድ]] ልጅ ማሊኽ እንደ ነበር እናቱም ዮጻዳቅ እንደ ተባለች የአርፋክስድ አባት ሴም በጻፈው መዝገብ እንደ ተገኘ ይጨምራል። ከዚህ በላይ፣ በ[[ኖህ]] ትዕዛዝ ሴምና መልከ ጼዴቅ አብረው ወደ [[አራራት]] ሔደው የ[[አዳም]]ን ሬሳ ከ[[ኖህ መርከብ]] አወጡት። ከዚያ በሗላ፣ በመላዕክት ዕርዳታ ወደ ኢየሩስሌም ዞረው በ[[ጎልጎታ]] ኮረብታ ውስጥ አቀበሩት። አብራም በእግዚአብሔር ትዕዛዝ [[ይስሐቅ]]ን እንደ መሥዋዕት ወደ መሥዊያ ቦታ ባመጣው ጊዜ፣ የነበሩበት ኮረብታ ጎልጎታ ሲሆን የመልከ ጼዴቅ መሥዊያ ቦታ ነበር። ያንጊዜ የአሕዛብ ነገሥታት ስለ መልከ ጼዴቅ ዝና ሰምተው ለበረከት ወደርሱ መጥተው ነበር። እነዚህ ነገሥታት ሁሉ ወዲያው ከተማ ለመልከ ጼዴቅ ሠሩለት፣ ስሙን «እየሩሳሌም» አለው። ነጉሦቹም እንደሚከተሉ ይዘርዝራሉ፦ የ[[ጌራርጌራራ]] ንጉሥ [[አቢሜሌክ]]፣ የ[[ሰናዖር]] ንጉሥ [[አምራፌል]]፣ የዴላሳር ([[ኤላሳር]]) ንጉሥ [[አርዮክ]]፣ የ[[ኤላም]] ንጉሥ ኮሎዶጎምር፣ የሕዝብ ንጉሥ ቲዳል ([[ቲርጋል]])፣ የሰዶም ንጉሥ ቤራ (ባላ)፣ የ[[ገሞራ]] ንጉሥ ብርሳ፣ የ[[አሞራውያን]] ንጉሥ ስምዖን፣ የ[[ሳባ]] ንጉሥ ሲማይር፣ የቤላ ([[ዞዓር]]) ንጉሥ ቢስላህ፣ የ[[ደማስቆ]] ንጉሥ ህያር፣ እና የበረሃዎች ንጉሥ ያፍታር ናቸው። ከዚህም በኋላ የ[[ቴማን]] ንጉሥ ማዋሎን የመልከ ጼዴቅን በረከት ለማግኘት ወደ እየሩሳሌም ተጓዘ ይላል።<ref>[http://www.sacred-texts.com/chr/aa/aa2.htm ኪታብ አል-ማጋል] {{en}}</ref>
 
ተመሳሳይ ዝርዝሮች ''[[የመዛግብት ዋሻ]]'' እና ''[[የአዳምና ሕይዋን ትግል ከሠይጣን ጋራ]]'' በተባሉት መጻሕፍት ይገኛሉ። በ''አዳምና ሕይዋን ትግል'' ዘንድ የመልከ ጼዴቅ አባት የ[[አርፋክስድ]] ልጅ [[ቃይንም]] ነው። ''[[መጽሐፈ ንቡ]]'' የሚባለው ጽሑፍ እንደሚለው የቃይንም 2 ልጆች ሻላሕ ([[ሳላ (የኤቦር አባት)|ሳላ]]) እና ማላሕ ሲሆኑ፣ ማላሕ ዮጻዳቅን አግብቶ የመልከ ጼዴቅ ወላጆች ሆኑ።