ከ«ማርክ ትዌይን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 1 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q7245 ስላሉ ተዛውረዋል።
img
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:MarkTwain.LOCMark Twain Sarony.jpg|thumb|right|ማርክ ትዌይን]]
'''ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ''' ''([[እንግሊዘኛ]]: Samuel Langhorne Clemens)'' ወይም በብእር ስሙ '''ማርክ ትዌይን''' [[አሜሪካ]] ካፈራቻቸው ድንቅ ጸሃፍት መካካል የሚመደብ ደራሲ ነው። ትዌይን በኖቬምበር 1835 ዓ.ም. [[ሚዙሪ]] በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ተወለደ። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር የኖረው ሃኒባል በተባለች እና [[ሚሲሲፒ]] ላይ በተቆረቆረች ትንሽ ከተማ-አከል ቦታ ነው። አባቱ በ1847 ሲሞት ትዌይን ትምህርቱን በማቋረጥ በማተሚያ ቤት ውስጥ በሰልጣኝነት ተቀጠረ። ይህን ስራውን በ1857 በመተው የእንፋሎት [[ጀልባ]] ነጂ በመሆን መስራት ጀመረ። በዚሁ ስራ በቆየባቸው አመታት ነው ኋላ ላይ አድናቆትን ላተረፉለት የስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ የሚሆኑትን እውቀቶች ለማሰባሰብ የበቃው። እሱ ራሱም እንዳለው በዚሁ ስራ ላይ ነው "ማንኛውንም በልብ-ወለድ፣ በግለ-ታሪክም ሆነ በታሪክ ላይ ሊገኙ የሚችሉ የሰው ባህርያትን" ሊያጠና የበቃው።