ከ«ጉታውያን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot: Automated text replacement (-ሜስጶጦምያ +መስጴጦምያ)
No edit summary
መስመር፡ 7፦
በ2021 ዓክልበ. ግ. የአካድ ምጉሥ [[ሻርካሊሻሪ]] የጉቲዩምን ንጉሥ ሻርላግን ማረከው፤ በ2018 ግ. «ቀንበር (ግብር) በጉቲዩም አደረገበት» ይዘገባል። የአካድ መንግሥት ግን ከዚያ ድካም ለመሆን ሲጀምር፣ ጉታውያን በመስጴጦምያ ላይ ብዝበዛ ያድርጉ ነበር። ሠራዊት እንደ ደረሰባቸው ግን ሸሽተው ነበር። ከቤት ማለፍ ወይም እንኳን በእርሻ መግባት አስጊ ሁኔታ ስለ ሆነ፣ የመስጴጦምያ ምጣኔ ሀብት ተበላሸና ራብ ሆነ። በመጨረሻ፣ (2010 ግ.) ጉታውያን አካድን ወረሩና ገዙት። እንዲሁም የጉቲ ሠራዊት [[ኡሩክ]]ንና ኤላምን የዛኔ ወረሩ። የጉታውያን ንጉሥ [[ኤሪዱፒዚር]] እራሱን እንደ አካድ ነገስታት በማምሰል፣ ማዕረጉ 'የጉቲ ንጉሥና የ4 ሩቦች ንጉሥ' ተባለ። ጉታውያን በአገሩ ሁሉ የታሰሩት እንስሶች ከጉረኖአቸው ፈቱ። የጉታውያን ግዛት ለ[[እርሻ ተግባር]]ም ሆነ ለዜና መዋዕል ዝገባ ጥንቁቅ አልነበረም። በ''[[ሱመራዊው ነገሥታት ዝርዝር]]'' በአንዳንድ ቅጂ 25 ዓመታት ብቻ እንደ ገዙ የሚለው አቆጣጠር ትክክል ይመስላል፤ በትንሽ ጊዜ ውስጥ አገሩ በጽኑ ረሃብ ተያዘ። የኤላም ንጉሥ [[ኩቲክ-ኢንሹሺናክ]] ከጉታውያን ዘመን በፊትና በኋላ ስለሚታወቅ ለ124 አመታት (እንደ ሌላ ቅጂ) ሊሆን አይችልም።
 
በ1985 ዓክልበ. ያሕል፣ የኡሩክ ንጉሥ [[ኡቱ-ኸንጋልኸጛል]] የጉታውያን ንጉሥ [[ቲሪጋን]]ን እንዳሸነፈ ጉታውያንንም ከአገራቸው እንዳስወጣ ይባላል። ከዚህ በኋላ በ1984 ዓክልበ. የ[[ኡር]] [[ኡር-ናሙ]] ጉቲዩምን ዘረፈው። በ1676፣ 1674ና 1669 ዓክልበ. የ[[ባቢሎን]] ንጉሥ ሃሙራቢ ጉቲዩምን እንደገና ድል አደረገው።
 
በኋለኛ ዘመን፣ በ[[አሦር]] መንግሥት 'ጉቲ' የሚለው ስም ለ[[ሜዶን]] ይጠቅም ነበር። በ[[ፋርስ]]ም ንጉሥ [[ቂሮስ]] ዘመን፣ ታዋቂ አለቃ ጉባሩ 'የጉቲ አገረ ገዥ' ተባለ። በተራሮቹ የሚገኘው የዛሬው [[ኩርድ]] ሕዝብ ከጉቲዎቹ እንደ ተወለዱ የሚያምኑ ብዙ ናቸው።
 
{{S-start}}
{{S-bef | before=[[ኢሉሉ]]}}
{{S-ttl | title=የ[[ሱመር]] ነገሥታት | years=2010-1985 ዓክልበ. ግድም}}
{{S-aft | after=[[ኡቱ-ኸጛል]]}}
{{End}}
 
[[መደብ:የፋርስ ታሪክ]]