ከ«ቲፎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ይህ ይቅር
ኡፖስ፣ የተሳተው ተራራ
 
መስመር፡ 2፦
'''ቲፎን''' ([[ግሪክኛ]]፦ Τυφῶν /ቲውፎን/፤ ደግሞ '''ቲውፎስ፣ ቲውፈውስ፣ ቲውፋዖን''') በ[[ጥንታዊ ግሪክ]] [[አፈ ታሪክ]] አስፈሪና አደገኛ ጠላት ፍጡር ነበረ።
 
በግሪኮች ትውፊት ዘንድ፣ ከወገቡ በላይ እንደ ሰው ልጅ ቢመስልም በራሱ ፈንታ አንድ መቶ የ[[አርዌ]] ([[ደራጎን]]) ራሶች ከትክሻውና ከአንገቱ በቀሉ። (በሌላ ምንጭ ግን የሰው ልጅ ራስ ሲኖረው የደራጎን ራሶች ከጣቶቹ በቀሉ)። ከወገብ በታች ሁለንተናው የ[[እፉኝት]] ነበር (ወይም ከወገቡ በታች መቶ እፉኝቶች ነበር)። ሰውነቱ ደግሞ በብዙ [[ክንፍ]] ተሸፈነ፤ [[እሳት]]ም ከዓይኖቹ ወጥቶ አማልክት እንኳን ይፈሩ ነበር። በ[[ቲታኖማኪያ]] ጦርነት ዘመን ዚውስ [[ቲታኖች]]ን ስለ አሠራቸው፣ ቲፎን ዜውስን ለማጥፋት ሞከረ። ከትግል በኋላ ግን ዚውስ [[መብራቅ]]ን በመጣል አሸነፈውና ከ[[ደብረ አማናኤትና]] በታች (ወይም በ[[ታርታሮስ]]፣ በግሪኮች ዘንድ [[ገሐነም]] የመሰለ ቦታ) አጠመደው።
 
[[ሄሮዶቶስ]] እንዳመለከተው፣ በ[[ጥንታዊ ግብጽ]] አፈ ታሪክ የሚታወቀው [[ሴት (የግብጽ አፈታሪክ)|ሴት]] የተባለው ጣዖት ደግሞ በግሪኮች «ቲፎን» ይባል ነበር። ከሁሉ ጥንታዊ በሆነው ታሪካዊ ዘመን ከፈርዖኖቹ አስቀድሞ፣ እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ የሴት ዓላማ ወይም ምልክት «[[የሴት እንስሳ]]» (ምናልባት [[አዋልደጌሣ]]) ሲሆን ግሪኮች በኋላ ይህን ምልክት «ቲፎናዊ አውሬ» ይሉት ነበር። በትውፊቶቹ ዘንድ፣ ሴት ቀድሞ ወንድሙን [[ኦሲሪስ]]ን ([[ቄንቲያመንቱ]]ን) እንደገደለው ሁሉ፣ እንዲሁም ቲፎን ከቲታኖች ([[ጊጋንቴስ]]) ወገን አብሮ [[ዲዮኒስዮስ]]ን ወይም [[ኦሲሪስ አፒስ]]ን ገደለው። ሁለተኛውን ኦሲሪስ ስለ ገደለው ይህ ቲፎን ደግሞ እንደ ሴት (ጣኦቱ) ተቆጠረ።