ከ«ዳግማዊ ምኒልክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 40፦
ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ [[ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ]]ና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ [[ነሐሴ ፲፪]] ቀን [[፲፰፻፴፮]] ዓ.ም. [[ደብረ ብርሃን]] አካባቢ [[አንጎለላ]] ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በ[[አንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት]] ቤተ ክርስቲያን [[ክርስትና]] ተነሱ።
 
አያታቸው [[ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ]] የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ።እሳቸውአወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ [[ኢትዮጵያ]]ን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ይላል [[ጳውሎስ ኞኞ]] “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ (ገጽ ፲፪)
 
ምኒልክ እስከ ሰባት ዓመታቸው ድረስ [[መንዝ]] ውስጥ ጠምቄ በሚባል አምባ ከእናታቸው ዘንድ አደጉ።አያታቸው [[ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ]] ሲሞቱ የ[[ሸዋ]]ውን አልጋ የምኒልክ አባት ንጉሥ [[ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ]] ወረሱ።