ከ«ሥነ ቁጥር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 1 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q11205 ስላሉ ተዛውረዋል።
Robot: la:Arithmetica is a featured article; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Addition_Table.svg|250px|right|thumb|የመደመሪያ ሰንጠረዥ]]
'''ሥነ ቁጥር''' ወይንም በእንግሊዝኛ "አርቲሜቲክስ" ከሁሉ የሒሳብ ዘርፎች አንጋፋውና በሁሉም ሰው ጥቅም ላይ የሚውል ክፍል ነው። ሥነ ቁጥር የ[[ቁጥር|ቁጥሮችን]] ቅልቅል ውጤት የሚያጠና ሲሆን ብዙ ጊዜ ቁጥሮች [[መደመር|ሲደመሩ]]፣ [[መቀነስ|ሲቀነሱ]]፣ [[ማባዛት|ሲባዙ]]ና [[ማካፈል|ሲካፈሉ]] የሚያሳዩትን ባህርይ ይመረምራል። ሒሳብ ተማሪዎች የ[[ቁጥር ኅልዮት]] ውጤቶችን ከፍተኛ ሥነ ቁጥር በማለት ከለተ ተለት መደመርና መቀነስ ጥናቶች ይለዩዋቸዋል።
 
== ታሪክ ==
 
የሰው ልጆች ከጥንት ጀምሮ ሥነ ቁጥርን ተጠቅመዋል። ለምሳሌ አፍሪቃ ውስጥ የተገኘ 22፣000 ዓመት እንዳለው የሚቆጠር የአጥንቶች ቁርጥራጭ ለመቁጠርና ለመደመር ያገለግል እንደነበር ይጠቀሳል። በኋላም የ[[ግብጽ]] እና [[ባቢሎን]] ሰወች ቁጥርን መጻፍ እንደጀመሩና ይህን ፈጠራቸውን ለመደመርና ለመቀነስ እንደተገለገሉበት አሁን የተገኙ ቅርሶች ያስገነዝባሉ። የግብጽን የአጻጻፍ ስልት የተከተሉ [[ግሪክ (ሕዝብ)|ግሪኮችም]] በ[[ዩክሊድ]] እና ሌሎች የግሪክ ተማሪዎች አማካይነት ጥናቱን ለማሳደግ ችለዋል። ሆኖም እስከዚህ ዘመን የነበረው የቁጥር አጻጻፍ ስልት [[አቀማመጣዊ]] አልነበረም። ስለሆነም ለመደመርና ለመቀነስ፣ በተለይ ደግሞ ለማባዛትና ለማካፈል እጅግ የተወሳሰበና አሰልቺ ነበር።
 
የሒሳብና የሥነ ቁጥር እድገት ከፍተኛ እመርታ ያሳየው ሕንዳውያን ተማሪዎች [[ዜሮ]]ና [[አቀማመጣዊ]] አጻጻፍ ስልትን በ4ኛው ክፍለዘመን ሲፈለስፉ ነበር። ይህም አሁን በመላው አለም የሚሰራበት [[ህንዲ-አረብ ቁጥር]] (ማለቱ፡ 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 ) እንዲፈጠር አደረገ። [[ፊቦናቺ]] የተሰኘው የጣሊያን ነጋዴ የዚህን ድንቅ ቁጥር ቀመርና ጥቅም በመጽሐፉ በ1202 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ) በመጻፍና በአውሮጳ አገራት ሁሉ በማሰራጨት ታዋቂነቱ እንዲገን ሆነ።
 
የህንዲ-አረብ ቁጥር ስርዓት በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ የሒሳብ ትምህርት በአውሮጳ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረገ። ይሄው አዲሱ ስልት ለሒሳብ ጥናት መሰረት በመሆን የጥንቶቹን ሒሳብ ተማሪዎች ድንቅ ውጤቶች ከአዲሱ ስርዓት ጋር ሲነጻጻሩ እምብዛም ሆነው እንዲታዩ አደረጉ። የሂንዲ አረብ ቁጥር ስርዓት ለዘመናዊው የሒሳብ ትምህርት መነሳት ምክንያት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
 
== አስርዮሽ የቁጥር ስርዓት ==
[[አስርዮሽ]] የቁጥር ስርዓት አስር የተለያዩ ምልክቶችን በመጠቀም ቁጥሮችን የሚወከያ ስልት ነው። ከዚህ በተረፈ በአስርዮሽ ስርዓት [[አቀማመጣዊ]] ዋጋ ለያንዳንዱ ቁጥር ይሰጠዋል። በዚሁ ስርዓት ነጥብን በመጠቀም ክፍልፋዮች ከሙሉ ቁጥሮች ይለያሉ። ለምሳሌ '''507.36''' ፡ 5 መቶዎች፣ 0 አስሮች፣ 7 አንዶች ሲደመር 3 አስረኛወች፣ 6 መቶኛወች ን ለመወከል ይረዳል
 
== የሥነ ቁጥር ስሌቶች ==
መሰረታዊው የሥነ ቁጥር ስሌቶች [[መደመር]]፣ [[መቀነስ]]፣ [[ማባዛት]] እና [[ማካፈል]] ናቸው። ሌሎች ስሌቶችም በዚሁ ጥናት ስር ይካሄዳሉ። ለምሳሌ [[ፐርሰንቴጅ]]፣ [[ስኩየር ሩት]]፣ [[ማንሳት]]፣ [[ሎጋሪዝም]] ይገኛሉ።
 
 
=== መደመር (+) ===
 
መደመር ሁለት [[ተደማሪ]] ቁጥሮችን በማዋሃድ አንድ [[ድምር ውጤት]]ን ያገኛል። ከሁለት በላይ ቁጥሮችን መደመር ሁለት ሁለት ቁጥሮችን እየደጋገሙ ከመደመር ጋር አንድ ነው።
 
 
{{መዋቅር}}
 
[[Categoryመደብ:ሥነ ቁጥር|* ]]
 
{{Link FA|he}}
{{Link FA|la}}
{{Link FA|ru}}