ከ«ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: አዲስ ዘመን - Changed link(s) to አዲስ ዘመን (ጋዜጣ)
No edit summary
መስመር፡ 3፦
'''ኪዳኔ ወልደመድኅን''' ዓርብ ሌሊት [[ሐምሌ 2|ሐምሌ ፪]] ቀን [[1907|፲፱፻፯]] ዓ.ም [[ቡልጋ]] በ[[ከሰም ]]ወረዳ፤ [[የለጥ]] ቀበሌ፤ ልዩ ስሙ ቡሄ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ ከናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደጀን እና ከአባታቸው ከቀኛዝማች ወልደመድኅን አዩደረስ ተወልደው [[ነሐሴ 10|ነሐሴ ፲]] ቀን በጥምቀት ስም ኪዳነ ማርያም ተሰይመው [[የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ]][[ ቤተ ክርስቲያን]] [[ክርስትና]] ተነሱ። አባታችው ቀኛዝማች ወልደመድኅን ትውልድ ሃገራቸው [[ወበሪ]] ሲሆን፤ በዘመኑ የታወቁ ስመጥሩ ጠበቃ ነበሩ። ከወይዘሮ አስካለም ጋር የተገናኙት ሁለቱም እወረዳው ፍርድ ቤት [[ኮረማሽ]] ለየጉዳያቸው ሄደው እንደነበር ይነገራል። ኪዳነማርያምም እስከ ፲፪ ዓመት እድሜያቸው እዚያው ቡሄ አምባ ከአያታቸው አቶ ደጀን ደብሩ ቤት እንዳደጉና የቄስ ትምህርት ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደተከታተሉ ተጽፏል። ከዚህ በኋላ አባታቸው ቤት እያደጉ የ[[አማርኛ]]ና የ[[ግእዝ]] ትምህርት አጠናቀዋል።
 
አካለ መጠን ሲደርሱ በ፲፰ዓ መታቸው በ[[1925|፲፱፻፳፭]] ዓ.ም. [[አዲስ አበባ]] በ[[ክብር ዘበኛ]] ደንብ ተቀጥረው ወዲያው በ[[ቀኅሥ|ንጉሠ ነገሥቱ]] ትዕዛዝ ከስድሳ ዘጠኝ አዲስ ወታደሮች ጋር [[ባሌ]] ተመድበው እስከ [[1927|፲፱፻፳፯]] ዓ.ም ድረስ በተራ ወታደርነት ከዚያም በ ሃምሳ ዓለቃና በባሻነት ማእረግ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ [[ኢጣሊያ]] [[ኢትዮጵያ]]ን ሊወር ሲመጣ በ[[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ.ም በምስራቅ ደቡብ በ[[ደጃዝማች በየነ መርዕድመርድ]] እና በ[[ጄነራል አስፋው ወልደ ጊዮርጊስ]] መሪነት፤ የመጀመሪያ ልጃቸው ዓለማየሁ በተወለደ በዘጠኝ ቀኑ፤ [[ጥቅምት 11|ጥቅምት ፲፩]] ቀን [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ.ም ከ[[ጎባ]] ወደ [[ኦጋዴን]] ዘመቱ።
 
በዚህ ጦር ግንባር ፱ ወራት [[ለበሽሊንዲ]]፤ [[ዋቢ ሸበሌ]]፤ እና የመሳሰሉ ሥፍራዎች ከ እነ [[ባላምባራስ አየለ ወልደማርያም]] ጋር ሆነው ጠላትን ሲከላከሉ ከርመው ወደ ጎባ ተመለሱ። ከ[[ሰኔ]] [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ.ም ጀምሮ እስከ [[ሚያዝያ 23|ሚያዚያ ፳፫]] ቀን [[1929|፲፱፻፳፱]] ዓ.ም ከ[[አሩሲ]]፤ ከ[[ሲዳሞ]]፤ ከ[[ሐረር]]ና [[ኦጋዴን]] ወደ [[ጎባ]] በሃይል የመጣውን የጠላት ጦር በራሳቸው መሪነት ሲዋጉ ከርመው፤ መጨረሻ ላይ ተማም ከሚባለው ሥፍራ ላይ በተካሄደው ጦርነት ላይ ማምለጥ በማይቻልበት ኹኔታ በጠላት እጅ ወደቀው ተማረኩ። ጠላትም ለአምስት ወራት በጽኑ እሥራት ከያዛቸው በኋላ፤ በ[[ጥር]] ወር [[1930|፲፱፻፴]] ዓ.ም ጣሊያን መሳሪያ አስታጥቆ በሽፍን መኪና ከጎባ [[ወሊሶ]] አምጥቶ እስር ላይ አዋላቸው። ባሻ ኪዳኔም እዚሁ እስር ቤት እያሉ አብረዋቸው ከታሰሩት መሀል በምስጢር ቃለ መሃላ በመስጠት መቶ ሰዎች አሳብረው እዚያ ያለውን የጠላት ጦር ፈጅተው ለመሸፈት ከወሰኑ በኋላ ወደ ባላምባራስ (በኋላ ደጃዝማች) [[ገረሱ ዱኪ]] የሚላክ ሰው በማፈላለግ ላይ እያሉ ጠላት ሰምቶ ኖሮ አጥብቆ ይከታታላቸው ጀመር። ይኼን ሲገነዘቡ ነገሩን አብርደው ሲጠባበቁ ወደ ባላምባራስ ገረሱ የላኩት ብሩ የሚባለው መልክተኛ [[ጥር 15|ጥር ፲፭]] ቀን [[1930|፲፱፻፴ ]]ዓ.ም በጠላት እጅ ተይዞ ቀኑን ሙሉ ሲመረመር ዋለ። ባሻ ኪዳኔም በዚያው ዕልት ከምሽቱ ፪ ሰዐት ሲሆን በቃለ መሃላ ያደራጇቸውን ሰዎች በያሉበት እየሄዱ ከነመሳሪያቸው እየሰበሰቡ ሲያከማቹ የጠላትም ዘቦች ነቅተው በተንቀቅ ተሰልፈው ይጠብቋቸው ጀመር። ባሻ ኪዳኔ ግን ወገኖቻቸውን ሸልሉ ብለው ሲያሸልሉ የጠላት ዘቦች ተደናግጠው እንዲያውም 'እነሱ ሳይተኩሱ አትተኩሱ' የሚል ትእዛዝ አስተላልፈው ይጠባበቃሉ። ባሻ ኪዳኔም በዚህ ጊዜ ቃለ መሓላ ከሰጧቸው ፻ ሰዎች ውስጥ ፶፭ ወታደር ከነመሳሪያው፤ አራት ድግን መትረየስ፤ አስር ሣጥን ጥይት፤ ስድስት ሽጉጥ ከጠላት እጅ ነጥቀው እየተታኮሱ ሲወጡ የጠላት ኃይል ሃያ ወታደርና አንድ መትረየስ ከ ሁለት ሣጥን ጥይት ጋር ብቻ ገንጥሎ ሲያስቀርባቸው የተረፈውን መሳሪያና ወታደሮች ጋር ድል አድርገው ሸፈቱ። ወዲያውም ኩሳ ኪዳነምሕረት ከሚባል ሥፍራ ላይ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ተገናኙ።