ከ«ማኒሽቱሹ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «300px|thumbnail|«የማኒሽቱሹ ሐውልት»፣ በ[[ኪሽ ዙሪያ የርስት አከ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 5፦
በወንድሙ ሪሙሽ መሞት ማኒሽቱሹ ንጉሥ ሆነ። ዘመኑ በአንድ ጽላት እንዲህ ይተረካል፦
 
«ማኒሽቱሹ የዓለም ንጉሥ፣ [[አንሻን]]ንና [[ሺሪሁም]]ን (በአሁኑ [[ፋርስ]]) ሲያሸንፍ፣ የጦር መርከቦች የታችኛው ባሕር ([[የፋርስ ወሽመጥ]]) እንዲሻግሩ አደረገ። ባሕር ማዶ (በአሁኑ [[ኦማን]]?) የነበሩት ከተሞች 32 ሲሆኑ ተባብረው ለውግያ ተሠለፉበት፣ እርሱ ግን ድል አደረጋቸው። ከዚህ በላይ ከተማቸውን አሸንፎ ገዢዎቻቸውን መታቸው። ካስነሣቸው በኋላ አገራቸውን እስከ ማዕድን ቦታ ድረስ ዘረፈ። ከታችኛ ባሕር ማዶ ተራሮች፣ ጥቁር ድንጋያቸውን ቆፈረ፣ በጀልባዎቹ ላይ ጫናቸው፣ ወደ አካድ ወደቦች አመጣቸው፤ ሐውልትም አሠራ።» እንዲሁም «የማኒሽቱሹ ሐውልት» የሚሠራው ከጥቁር ድንጋይ ነው፤ ይህም ከኦማን ዘመቻ እንደ ተገኘ ይታስባል።
 
እንደ ወንድሙ ሪሙሽ ዘመን ግን የማኒሽቱሹ ዘመን በአመጽ እንደ ተሞላ ይመስላል። ሪሙሽም በግድያ እንደ ሞተ፣ ማኒሽቱሹ ደግሞ በራሱ ሎሌዎች እጅ ተገደለ። ልጁ [[ናራም-ሲን]] ተከተለው።