ከ«አምባሰል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 3 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q2841469 ስላሉ ተዛውረዋል።
Robot: Removing selflinks
መስመር፡ 22፦
የዓፄ [[ይኩኖ አምላክ]] እናት ከ[[ሰገረት]] እንደመጣች ሲነገር፣ አባቱ ደግሞ ከዚህ ቦታ እንደመነጨ ይጠቀሳል። በዚህ ምክንያት ይመስላል፣ የዚህ አምባ ባለስልጣኖች [[ጃንጥራር]] በሚል ልዩ ማዕረግ ከጥንት ጀምሮ እስከ ንጉሳዊው ስርዓት ፍጻሜ አካባቢውን ያስተዳድሩ ነበር ( ከቅርብ ምሳሌ [[እቴጌ መነን]] የ[[ጃንጥራር አስፋው]] ልጅ ነበሩ)። የይኩኖ አምላክ የልጅልጅ የሆኑት ዓፄ [[ጅን አሰገድ]] ተገዳዳሪ የነገሥታት ወንድ ልጆችን በዚህ ወረዳ በሚገኘው [[አምባ ግሸን]] ላይ ማሳሰር እንደጀመሩ ታሪክ ጸሐፊው [[ዋሊስ ባጅ]] ይጠቅሳል። እኒህ የሚታሰሩት ሰዎች [[ቤተ እስራኤል]] ወይንም በቀላሉ [[እስራኤል|እስራኤላውያን]] ይባሉ ነበር። ስለሆነም ከአምባ ግሸን አጠገብ የሚገኘው ተራራ አምባ እስራኤል ወይንም [[አምባ ሰል]] መባል ጀመረ<ref> Whiteway, R. S. (Richard Stephen), ''The Portuguese expedition to Abyssinia in 1541-1543 as narrated by Castanhoso'', London, Printed for the Hakluyt Society, page ix,(1902) ([http://www.archive.org/stream/portugueseexpedi00whitrich#page/n11/mode/2up በኢንተርኔት ]</ref> ።
 
በ1682 ዓ.ም. የታተመው የ[[የኢትዮጵያ ካርታ 1690|ቪቼንዞ ኮሮኔሊ ካርታ]] አምባ ሰልን በ[[አምኅራ]] ግዛት የሚገኝ ተራራ እና የንጉሳዊ ቤተሰቦች መያዣ እንደሆነ ያሳያል<ref>[[የኢትዮጵያ ካርታ 1690]]</ref>። ቆይቶ፣ የጣሊያን ወራሪዎች ከመምጣታቸው በፊት አምባሰል ከተራራ ስምነት ባሻገር የ[[አስተዳደር ክፍል]] ስም በመሆን ከዋና ከተማው [[ማርየ ስላሴ]] ይተዳደር ነበር። በጣሊያን ወረራ ጊዜ የአምባሰል ዋና ከተማ [[ጎልቦ]] ሆነ፣ ለዚህም ምክንያቱ ለ[[አዲስ አበባ]] - [[መቀሌ]] መንገድ ጎልቦ ስለሚቀርብ ነበር። ጣሊያኖች ሲባረሩ ዋና ከተማው [[ውጫሌ]] ተብሎ በወረዳነቱ ጸና። ቀጥሎ የ[[አውርጃ]] ስርዓት ሲተገበር [[አምባሰል]]፣አምባሰል፣ [[ተሁለደረ]] እና [[ወረ ባቦ]] አንድ ላይ ሆነው የ[[አምባሰል አውራጃ]]ን መሰረቱ። የአውራጃው ዋና ከተማ [[ሐይቅ]] ነበር። የ[[ደርግ]] ስርዓት በአውራጃነቱ ካስቀጠለው በኋላ የ[[ዞን]] ስርዓትን ሲተገብር አውራጃውን ወደ መሰረቱት ወረዳዎች በመክፍል አምባሰል በወረዳነቱ ጸና<ref>[https://docs.google.com/viewer?a=v&q=cache:GYBgnDeh6hgJ:etd.aau.edu.et/dspace/bitstream/123456789/1103/1/DANIEL%2520TESFAYE.pdf+&hl=en&gl=us&pid=bl&srcid=ADGEEShjt1WunkiM-hPYTNcyNX7ICF8EG-VHo99TRd8eOSKvAUQVS7vFlszsbgi70jEpE8ddyJHalKtGeGWRE50i8DOaQEUsgG0ZFyc89-iW2lg7yhVgg2bZ8I9ABH40ZhxLEtcVMbrN&sig=AHIEtbSCSMwcF7m3UEBZzz30YKukDMAXog ኢንተርኔት]</ref>። ወረዳው በአሁኑ ወቅት 23 [[ቀበሌ|ቀበሌዎችን]] አቅፎ ይገኛል። ይሄው ከበፊት ከነበረው 34 ጭቃዎች ዝቅ ያለ ነው።
 
== ህዝብ ቆጠራ ==