ከ«ፊሊፒንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 4፦
ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ብሔሮች በፊሊፒንስ ይገኛሉ። ከባህሎቹ ልዩነት የተነሣ፥ በደሴቶቹ ላይ ብዙ ልማዳዊ የ[[ሙዚቃ]] አይነቶች አሉ። ከነዚህ ልዩ ልዩ ሙዚቃዊ ፈሊጦች ጋራ በፊሊፒኖ ባህል የተለያዩ ልማዳዊ ጭፈራ አይነቶች ይሄዳሉ። ለምሳሌ [[ቲኒክሊንግ]]፣ [[ካሪኖሳ]] እና [[ሲንግኪል]] የተባሉ ጭፍራዎች አሉ። በፊሊፒንስ አንዳንድ ጎሣ የተወሳሰበ ብርድ ልብስ ሽመና ስለ መሥራታቸው ዕውቅና አላቸው። ሌሎች ጎሣዎች ጌጣጌጥ ከ[[ሉል]]ና ከቀይ መንቁራ ወዘተ. ይሠራሉ። ከሁሉ ቀላል ኑሮ በሩቅ ደን ቦታዎች የሚገኙ ጎሣዎች እስካሁን ድረስ በትንፋሽ የሚነፋ ፒፓ (ፍላጻን ለመውረር) ለማደን እንደ መሣርያ ይጠቅማሉ። በፊሊፒንስ ብቻ የሚማሩ የትግል (ቡጢ) ሥነ ሥርዐቶች ለምሳሌ [[አሚስ]] እና [[ኤስክሪማ]] ይታወቃሉ።
 
ጨዋታ በፊሊፒንስ በተለይም [[ቢሊያርድስ]] ([[ከረንቦላ]]ን የሚመስል)፣ [[ቦውሊንግ]]ና [[ሠንተረዥሰንጠረዥ]] (ቼዝ) ይወደዳሉ። [[እግር ኳስ]]ና [[ቡቅሻ]] ደግሞ በጣም ይወደዳሉ።
 
90 ከመቶ የፊሊፒንስ ኗሪዎች [[የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን]] ምዕመናን ናቸው፣ በየከተማውም ስፓኒሾች ከድንጋይ የሠሩ አቡያተ ክርስቲያናት አሁንም አሉ። ሌላ 5 ከመቶ እስላሞች ናቸው፣ የቀሩትም 5 ከመቶ አረመኔ ልማዶች ወይም ሌላ እምነት የሚከተሉ ናቸው።