ከ«መቅደላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
Robot-assisted disambiguation: ደብረ ታቦር - Changed link(s) to ደብረ ታቦር (ከተማ)
መስመር፡ 21፦
==መቅደላ አምባ እና [[ዓፄ ቴዎድሮስ]]==
 
መቅደላ አምባ ለመድረስ ከ[[ደሴ]] ከተማ በስተምዕራብ ፻፳፰ ኪ/ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው የተንታ ከተማ በስተሰሜን ምስራብ ፳፱ ኪ/ሜ መጓዝን ይጠይቃል፡፡ ጥንት ከመቅደላ [[ደብረ ታቦር (ከተማ)|ደብረ ታቦር]] ከዚያም ወደጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚያዘልቅ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ጐብኝዎች የሚታወቅ የእግር መንግድ ነበር፡፡ ግን ልክ እንደ ጥንታዊው የ[[ላሊበላ]] ሰቆጣ መንገድ ሁሉ መስመሩ ከተዘጋ ዘመናት ተቆጥረዋል።
 
መቅደላ ሲነሳ [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] መታወሳቸው የማይቀር ነው፡፡ የመቅደላ አምባ ዙሪያ ገባውን ከርቀት ለመቆጣጠር የሚያስችል በመሆኑና በዘመኑ የፖለቲካ ከርሰ-ምድር ሁነኛ ሥፍራ ላይ በመገኘቱ ከፍተኛ ቁልፋዊ ጥቅም ነበረው፡፡ ይህ ጠቀሜታ ደግሞ በወቅቱ [[ኢትዮጵያ]]ን አንድ ለማድረግ ለሚጥር ንጉሥና ባለሟሎቹ የሚሰወር አልነበረም።
 
በንጉሠ ነገሥቱ የፖለቲካ ሥልጣን መባቻ ለሰባት ወራት የተካሄደው የ[[ወሎ]] ዘመቻ የተጠናቀቀውም በመቅደላ መያዝ ነበር፡፡ [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ከ[[ጎንደር]] በኋላ የሥልጣን ማእከላቸውን ለጊዜው ወደ [[ደብረ ታቦር (ከተማ)|ደብረ ታቦር]] ከዚያም ወደመቅደላ በማዞር ለተቀረው ግዛት ዓርዓያ ሊሆን የሚችል የአስተዳደር ሥርዓት ለማቆም ጥረት የጀመሩት በዚሁ ሥፍራ ነበር፡፡ በርካታና የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ብዛት ያላቸው ገድሎች፣ መጻሕፍትና ድርሳናት እንዲሁም የንጉሠ ነገሥቱ የግል የክብር ዕቃዎች በሥርዓት ተሰድረው ይቀመጡ የነበረው በመቅደላ ግምጃ ቤት ነበር።
 
በዘመኑ ፲፭ መድፎች፣ ፯ ሞርታሮች፣ ፲፩ ሺ ፷፫ የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ ፰፻፸፭ ሽጉጦችና ፬፻፹፩ ሳንጃዎች፣ ፭፻፶፭ የመድፍና የሞርታር አረሮች እንዲሁም ፹፫ ሺ ፭፻፷፫ የተለያዩ ጥይቶች በመቅደላው ግምጃ ቤት እንደነበሩ መረጃዎች ይገልፃሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ለታሪክ መዘክርነት በቦታው ከሚገኙት ቅርሶች አንዱ ‘ሴባስቶፖል’ የተባለው የንጉሠ ነገሥቱ ትልቅ መድፍ እና [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ጊዜያዊ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽና የመቃብር ቦታዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍቱ፣ ድርሳናቱ፣ የወርቅና ብር ዋንጫዎች፣ አክሊሎችና ሌሎች የንጉሠ ነገሥቱ የግል ሀብቶች የነበሩ ቅርሶች ሁሉ ከመቅደላው ጦርነትና ከ[[ዓፄ ቴዎድሮስ]] እረፍት በኋላ በደላንታ ሜዳ ለጨረታ ተሰጥተው በ ናፒዬር የተመራው የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] ሠራዊት ተቀራምቷቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ከንጉሠ ነገሥቱ አናት ላይ የተሸለተውን ሹሩባ ፀጉር ጨምሮ ሌሎች ቅርሶች በ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] አገር የተለያዩ የሥነ-ቅርስ መዘክሮች ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ።