ከ«ዳግማዊ ምኒልክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
Robot-assisted disambiguation: ደብረ ታቦር - Changed link(s) to ደብረ ታቦር (ከተማ)
መስመር፡ 84፦
የመጀመሪያውን የመተናኮል ተግባር የጀመሩት ዓፄ ዮሐንስ ሲሆኑ፣ የንጉሥ ምኒልክን ገባር የበጌ ምድሩን ገዥ ራስ ወልደ ማርያምን ለማሳመን ከዘመቱ በኋላ [[ጎጃም]]ን አሳምነው ወደ [[ሸዋ]] ለመምጣት ዘቢጥ ላይ ሲደርሱ ከወደኋላ የ[[ቱርክ]] ጦር መጣ የሚባል ወሬ ስለሰሙ ወደ[[ትግራይ]] ተመለሱ። ይማም አባ ዋጠውም (ንጉሥ ሚካኤል) ምኒልክን ከድተው ወደ ዓፄ ዮሐንስ ሲገቡ ምኒልክ ገስግሰው [[የጁ]] ላይ ደርሰውባቸው እጃቸውን ይዘው አስረው ወደሸዋ ሰደዷቸው፡
 
ምኒልክ ወዲያው መልሳቸውን በ[[ጎጃም]] አድርገው [[በጌ ምድር]] ዘመቱና [[ደብረ ታቦር (ከተማ)|ደብረ ታቦር]] ላይ ሳሉ ዓፄ ዮሐንስ መምጣታቸውን ሲሰሙ እንደገና ወደ ጎጃም ተሻገሩ። ወዲያውም ወደሸዋ ተመለሱ። ይሄኔ ነው ወይዘሮ ባፈና ምኒልክን ከድተው ካማቻቸው ከይማሙ መሐመድ አሊ ጋር ተማምለው ወደዓፄ ዮሐንስ መላላክ ጀምረው ነበር።እንዲሁም አጎታቸው የ[[ቡልጋ]]ው ገዥ [[መርዕድ አዝማች]] ኃይለ ሚካኤልም ሸፍተው [[አንኮበር]]ን ይዘው ነበር።
 
መርዕድ አዝማቹ ሚጣቅ አፋፍ ላይ ሲያዙ ወይዘሮ ባፈና ደግሞ [[መርሐ ቤቴ]] ላይ ኮላሽ አምባ እምቢላው ሥፍራ ላይ የተከተሏቸው ወታደሮች አሠሯቸው። ንጉሡ ይማሙ መሐመድ አሊን ለመያዝ በግስጋሴ ተከታትለው ሲደርሱበት አምልጦ በመሄዱ ተናደው ከተማውን [[ደሴ]]ን አቃጠሉት።
 
ዓፄ ዮሐንስ [[ደብረ ታቦር (ከተማ)|ደብረ ታቦር]] ላይ ሳሉ ከሸዋ ከሦስት ወገን መልእክት ይደርሳቸው ነበር።
 
በአንዱ ወገን አቤቶ መሸሻ ሰይፉ እርስዎ ከመጡ በሸዋ የኔ ወገን ነውና የሚበዛው ከንጉሥ ምኒልክ ምንም የሚሰጉበት ነገር የለም ብሎ ልኮላቸዋል።