ከ«ዴቪድ ሁም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 79 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q37160 ስላሉ ተዛውረዋል።
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:David Hume.jpg|thumb|right|ዴቪድ ሁም ]]
 
'''ዴቪድ ሁም''' ([[ግንቦት 7]] [[1711]] - [[ነሐሴ 25]] [[1776]]) የነበረ የ[[ስኮትላንድ]] [[ታሪከኛ]] እና [[ፈላስፋ]] ነበር። <ref name=TIME>{{cite book|last=Gay|first=Peter|coauthors=Time-Life Books|title=Age of Enlightenment|year=1966|publisher=Time|pages=53|chapter=In Search Of An Ideal Society}}</ref> ሁም በዘመኑ ይታወቅ የነበረው በታሪክ ተመራማሪነት ነበር። የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] [[ታሪክ]] የሚሉ ትላልቅ መጻሕፍትን በዘመኑ ደርሶ ለህትመት አብቅቶ ነበር። አሁን ግን ሁም የሚታወቀው በዋና [[ፈላስፋ]]ነቱ ነው።
 
በፍልስፍና መጽሕፉ ላይ እንደሚያስረዳ ብዙው የሰው ልጅ አምኖ የሚቀበላቸው ነገሮች በ [[አምክንዮ|በምክንያት]] የተደገፉ አይደሉም። ይልቁኑ ከ[[ስሜት]]ና [[ደመነፍስ]] የሚመነጩ ናቸው። ለምሳሌ አምክንዮ የአንድ ነገር መንስኤ ሌላ ነገር ነው ብሎ አይናገርም። ነገር ግን አንድ ክስተት ሲፈጠርና ከዚያ ቀጥሎ ሌላ ክስተት ሲፈጠር ስናይ የመጀመሪያው ክስተት ለሚቀጥለው ክስተት መንስኤ ነው ብለን በ"ስሜት" እንደመድማለን። በተመሳሳይ አንድ ሰው [[ሰናይ]] ግለሰብ እንደሆነ ምክንያት አይነግረንም። ይልቁኑ ያ ሰው ደግና ተግባቢ ሆኖ ስናየው በስሜት ሰናይ ነው እንላለን። እኒህ ነገሮች ከምክንያት አይመነጩም ብሎ ሁም ስለሚያምን '''ተጠራጣሪ''' ወይንም '''ኢ-ምክንዮት''' ፈላስፋ ተብሎ ይታወቃል።