ከ«ዳግማዊ ምኒልክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 1 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q244748 ስላሉ ተዛውረዋል።
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
መስመር፡ 73፦
ተቃራኒያቸውን አቶ በዛብህን ጋዲሎ ላይ ድል ካደረጉ በኋላ፣ ንጉሥ ምኒልክ ታማኞት የ[[ሸዋ]] መኳንንትን በሚሠበስቡበትና በሚያዳብሩበት ጊዜ ትኩረታቸውን [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] አሲዘው በ[[መርሐ ቤቴ]] አውራጃ በደጃዝማች ወልደ ሚካኤል ሥር ያስጠብቋቸው የነበሩትን አጎታቸውን [[መርዕድ አዝማች]] ኃይለ ሚካኤልን ነጻ ለማውጣት [[ግንቦት 21|ግንቦት ፳፩]] ቀን [[1859|፲፰፻፶፱]] ዓ/ም ከ[[ልቼ]] ዘመቱ። ያላንዳች ተኩስ አጎታቸውን ካስለቀቁ በኋላ ወደ ልቼ ተመልሰው መርዕድ አዝማቹ የ[[ቡልጋ]]ን ግዛት ተሰጣቸው።
 
በ[[ሚያዝያ 7|ሚያዝያ ፯]]ቀን [[1860|፲፰፻፷]] ዓ/ም [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]]ን ጦር [[መቅደላ]] ላይ ገጥመው መሞታቸው ሲሰማ ንጉሥ ምኒልክ ወደ [[ወሎ]] ዘምተው ባላባቶቹን አስገብረው፣ [[ወረይሉ]]ን ቆርቁረው ወደ ሸዋ ተመለሱ። በኋላም አንደኛው የወሎ ባላባት መሐመድ አሊ (በኋላ [[ንጉሥ ሚካኤል]]) ገቡላቸውና ይማሙ ብለው ወሎን በሙሉ ሰጧቸው። ለመተማመኛም የወይዘሮ ባፈናን ልጅ ወይዘሮ ማናለብሽን ልጅ ዳሩላቸው።
 
የ[[ትግራይ]] ደጃዝማች ካሳ (በኋላ [[ዮሐንስ ፬ኛ|ዓፄ ዮሐንስ]] [[ሐምሌ 4|ሐምሌ ፬]] ቀን [[1864|፲፰፻፷፬]] ዓ/ም የቴዎድሮስን ተከታይ [[ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ]]ን ተዋግተው ድል ስላደረጉ ዮሐንስ ፬ኛ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ።
 
==ንጉሡ እና ዓፄ ዮሐንስ==
ምኒልክ እና ዮሐንስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ ጠባያቸው የተለያየ እና እርስ በርስ የማይተማመኑ ነበሩ። ዓፄ ዮሐንስ ማቹን ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስን ሊወጋ የመጣውን የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] ሠራዊት በመርዳት ከሸኚ እና ስንቅ ጋር በግዛታቸው እንዲያልፍ በማድረጋቸው ወሮታውን ከድሉ በኋላ በዘመናዊ መሣሪያ፤ መድፍ እና ጥይት አበልጽጓቸው ሲሄድ በጊዜው ከነበሩት መሪዎች ሁሉ የላቀ ኃይል ለማግኘትና ያስከተለውንም የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ እጃቸው ለማስገባት አመቸላቸው።
 
ንጉሥ ምኒልክ ደግሞ ጊዜያቸው እስኪደርስ፤ ኃይላቸውን በዘመናዊ መሣሪያዎች እስከሚያዳብሩና ለንጉሠ ነገሥትነቱ ሥልጣን እስከሚዘጋጁ ድረስ ግዛታቸውን በደቡብ እና በምዕራብ አቅጣጫ እያስፋፉ በዘዴ ለንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ታማኝና የበታች መስለው መኖርን ያዙ።
መስመር፡ 132፦
==ከንጉሥነት ወደ ንጉሠ ነገሥትነት==
[[ስዕል:MENELIK II SAHALA MARIEN RULER OF ETHIOPIA 1844-1913 jpg.jpg|left|thumb|250px| ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ ]]
ዓፄ ዮሐንስ በተለያየ ጊዜ፣ ባንድ በኩል የምስር ([[ግብጽ]]) ሠራዊት በግዛታቸው በ[[ምጽዋ]] በኩል፤ ባንድ በኩል ደርቡሾች በሌላ በኩል ደግሞ የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]]ን ድጋፍ የያዙት [[ኢጣልያ]]ኖች ከ[[አሰብ]] በቶሎ አልፈው ቤይሉል የሚባለውን የባሕር ጠረፍ ያዙ። ከነኚህ የውጭ ቀማኞች ጋር ክፉኛ ፍልሚያ ይዘው አንዳንዴ ሲያሸንፉ አንዳንዴም ሲገፏቸው ኖሩ።
 
በ[[፲፰፻፹፩]] ዓ/ም [[ደምቢያ]] ሣር ውሐ ላይ ደርቡሾች ከ[[ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት]] ጋር ገጥመው አሸንፈው የፈጁትን የኢትዮጵያን የክርስቲያን አጽም አይተው እጅግ አዘኑ። ከዚያም ወደ[[መተማ]] ገሠገሡ። አሳባቸው [[መተማ]]ን አጥፍተው ወደ ትልቁ ከተማ [[ኦምዱርማን]] ለመሄድ ነበር። [[መጋቢት 1|መጋቢት ፩]] ቀን [[፲፰፻፹፩]] ዓ/ም ቅዳሜ ጦርነት ገጥመው የከተማውን ቅጥር ጥሰው ከገቡ በኋላ በጠመንጃ ጥይት ተመተው ቆሰሉ። ወሬውም ያንጊዜውን በየሠልፉ ውስጥ ሲሰማ መኳንንቱም ወታደሩም ከቅጥሩ ውስጥ እየወጡ መሸሽ ጀመሩ። በማግሥቱ [[እሑድ]] [[መጋቢት 2|መጋቢት ፪]] ቀን አረፉ። ደርቡሾቹም የንጉሠ ነገሥቱን ሬሳ ከማረኩ በኋላ ራሳቸውን ቆርጠው በእንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ መንደር ለመንደር እያዞሩ ሲያሳዩ ዋሉ።