ከ«ፀሐይ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Bot: Migrating 210 interwiki links, now provided by Wikidata on d:q525 (translate me)
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
መስመር፡ 16፦
የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ (''mass'') ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው።
 
ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል (''disk'') መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት (''supernatural phenomenon'') ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ [[ሜክሲኮ]]) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን (''summer solstice'') ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። (በጣም ጐልተው ከሚታዩ ሜጋሊቶች ውስጥ ጥቂቱ በ [[ናባታ ፕላያ]]፣ [[ግብጽ]]፣ እና በ [[ስቶንሄንጅ]]፣ [[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]]፣ ውስጥ ይገኛሉ።)
 
ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን (''ecliptic'') ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ።